Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መዝሙር 51:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 አቤቱ፥ እንደ ቸርነትህ መጠን ማረኝ፥ እንደ ምሕረትህም ብዛት መተላለፌን ደምስስ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 እኔ መተላለፌን ዐውቃለሁና፤ ኀጢአቴም ዘወትር በፊቴ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 እኔ ስሕተቴን ዐውቃለሁ፤ የኃጢአቴንም ብዛት ዘወትር እገነዘባለሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ከመ​ል​ካም ይልቅ ክፋ​ትን፥ ጽድ​ቅ​ንም ከመ​ና​ገር ይልቅ ዐመ​ፃን ወደ​ድህ።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 51:3
12 Referencias Cruzadas  

የእስራኤል ዘር ከባዕድ ሕዝቦች ሁሉ ራሳቸውን ለዩ፥ ቆመውም ኃጢአታቸውንና የአባቶቻቸውን በደል ተናዘዙ።


እርሱም በሰው ፊት እየዘመረ፦ እኔ በድያለሁ፥ ቀናውንም አጣምሜአለሁ፥ የሚገባኝንም ቅጣት አልተቀበልሁም፥


ኃጢአቴን ለአንተ አስታወቅሁ፥ በደሌንም አልሸፈንሁም፥ መተላለፌን ለጌታ እነግራለሁ አልሁ፥ አንተም የኃጢአቴን ሸክም ተውህልኝ።


እኔስ ለመውደቅ ተቃርቤአለሁና፥ ቁስሌም ሁልጊዜ በፊቴ ነውና።


አቤቱ፥ አንተ ርኅራኄህን ከእኔ አታርቅ፥ ቸርነትህና እውነትህ ዘወትር ይጠብቁኝ።


እኔስ፦ “አቤቱ፥ ማረኝ፥ አንተን በድያለሁና ነፍሴን ፈውሳት” አልሁ።


ጥፋቱን የሚሰውር አይለማም፥ የሚናዘዝባትና የሚተዋት ግን ምሕረትን ያገኛል።


መተላለፍህን፦ ስለ እኔ ስል የምደመስስ እኔ ነኝ፤ ኃጢአትህንም አላስብም።


ዓመፃችን በአንተ ፊት በዝቶአልና፥ ኃጢአታችን መስክሮብናልና፥ ዓመፃችን ከእኛ ጋር ነውና፥ በደላችንን እናውቃለንና።


ከትንሽነታችን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እኛና አባቶቻችን በአምላካችን በጌታ ላይ ኃጢአት ሠርተናልና፥ የአምላካችንንም የጌታን ድምፅ አልሰማንምና፥ በእፍረታችን እንጋደም፥ ውርደታችንም ይሸፍነን።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos