ዘሌዋውያን 11:47 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህም በርኩስና በንጹሕ መካከል፥ በሚበላና በማይበላ ሕይወት ባለው ፍጥረት መካከል ለመለየት ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህም በርኩሱና በንጹሑ መካከል፣ እንዲሁም ሕይወት ካላቸው ፍጥረታት የሚበሉትንና የማይበሉትን ትለያላችሁ።’ ” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጹሕ በሆነውና ንጹሕ ባልሆነው መካከል ያለውን ልዩነት ለማወቅ፥ ይኸውም በሚበሉትና በማይበሉት እንስሶች መካከል ያለውን ልዩነት ለመረዳት ብርቱ ጥንቃቄ አድርጉ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በርኩስና በንጹሕ መካከል፥ የሕይወት ነፍስ ካላቸውም በምትበሉትና በማትበሉት መካከል እንድትለዩ ነው።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በርኩስና በንጹሕ መካከል፥ የሕይወት ነፍስ ካላቸውም በምትበሉትና በማትበሉት መካከል እንድትለዩ ነው። |
ካህናቶችዋም ሕጌን ጥሰዋል፥ ቅዱሳት ነገሮቼንም አርክሰዋል፤ ቅዱስ በሆነ ነገርና በረከሰ ነገር ላይ ልዩነትን አላደረጉም፥ በርኩስ ነገርና በንጹሕ ነገር መካከል ያለውን ልዩነት አላስታወቁም፥ ከሰንበቶቼ ዓይናቸውን ሰወሩ፥ እኔም በመካከላቸው ረከስሁ።