እኔም እንዲህ አልሁ፦ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ወይኔ! እነሆ፥ ሰውነቴ አልረከሰችም፥ ከልጅነቴ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ፥ የሞተ ወይም እንስሳ የገደለውን ከቶ አልበላሁም፥ ርኩስም ሥጋ በአፌ ውስጥ አልገባም።
ዘሌዋውያን 11:39 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ለምግብነት ከምታውሉት እንስሳ የሞተ ቢኖር፥ በድኑን የሚነካ ሁሉ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘እንድትበሉ ከተፈቀደላችሁ እንስሳት አንዱ ቢሞት፣ በድኑን የሚነካ ማንኛውም ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ከሚበሉትም ቢሆን ማናቸውም እንስሳ ቢሞት የሚነካው ሁሉ እስከ ምሽት ርኩስ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ለመብል ከሚሆኑላችሁ እንስሳት የሞተ ቢኖር፥ በድኑን የሚነካ ሁሉ እስከ ማታ ርኩስ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለመብል ከሚሆኑላችሁ እንስሶች የሞተ ቢኖር፥ በድኑን የሚነካ ሁሉ እስከ ማታ ርኩስ ነው። |
እኔም እንዲህ አልሁ፦ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ወይኔ! እነሆ፥ ሰውነቴ አልረከሰችም፥ ከልጅነቴ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ፥ የሞተ ወይም እንስሳ የገደለውን ከቶ አልበላሁም፥ ርኩስም ሥጋ በአፌ ውስጥ አልገባም።
ከሚንቀሳቀሱት ሁሉ መካከል በእናንተ ዘንድ ርኩሶች የሆኑት እነዚህ ናቸው። ከእነርሱም የሞተውን የሚነካ ሁሉ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል።
ከበድኑም የሚበላ ልብሱን ያጥባል፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ እንዲሁም በድኑን የሚያነሣ ልብሱን ያጥባል፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል።
ካህኑም አንደኛውን ለኃጢአት መሥዋዕት፥ ሌላውንም ለሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ ያቀርባቸዋል፤ ካህኑም በጌታ ፊት ስለ ፈሳሹ ነገር ያስተሰርይለታል።
የሞተውን ወይም አውሬ የገደለውን የሚበላ ሰው ሁሉ፥ የአገሩ ተወላጅ ወይም እንግዳ ቢሆን፥ ልብሱን ያጥባል፥ በውኃም ይታጠባል፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ ከዚያም በኋላ ንጹሕ ይሆናል።
ከአሮን ዘር ማናቸውም ሰው የለምጽ ደዌ ወይም ፈሳሽ ነገር ያለበት፥ ንጹሕ እስኪሆን ድረስ ከተቀደሱት ነገሮች አይብላ። በበድን፥ ወይም ዘሩ በሚፈስስበት ሰው የረከሰውን ነገር የሚነካ፥
በተንጣለለው ሜዳ በሰይፍ የተገደለውን ወይም የሞተውን በድን ወይም የሰውን ዐፅም ወይም መቃብር የሚነካ ማናቸውም ሰው ሰባት ቀን ርኩስ ይሆናል።