ከመጋረጃው ውጭ ባለው በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በምስክሩ ታቦት ፊት አሮንና ልጆቹ ከማታ እስከ ማለዳ ድረስ በጌታ ፊት ያሰናዱት፤ በእስራኤል ልጆች ዘንድ በትውልዳቸው የዘለዓለም ሥርዓት ይሁን።”
ዘሌዋውያን 10:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እንዳትሞቱ ወደ መገናኛው ድንኳን ስትገቡ አንተና ከአንተ ጋር ያሉት ልጆችህ የወይን ጠጅና የሚያሰክርን መጠጥ አትጠጡ፤ ይህም ለልጅ ልጃችሁ የዘለዓለም ሥርዓት ነው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እንዳትሞቱ አንተና ልጆችህ ወደ መገናኛው ድንኳን በምትገቡበት ጊዜ የወይን ጠጅ ወይም ሌላ የሚያሰክር መጠጥ አትጠጡ፤ ይህም በልጅ ልጃችሁ ዘንድ የሚጠበቅ ዘላለማዊ ሥርዐት ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አንተና ልጆችህ የወይን ጠጅ ወይም ሌላ የሚያሰክር መጠጥ ጠጥታችሁ ወደ መገናኛው ድንኳን እንዳትገቡ ተጠንቀቁ፤ ይህን ብታደርጉ ትሞታላችሁ፤ ይህም ሕግ ከእናንተ በኋላ በሚነሣውም ትውልድ ዘንድ ሁሉ ተጠብቆ መኖር አለበት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እንዳትሞቱ ወደ ምስክሩ ድንኳን ስትገቡ ወይም ወደ መሠዊያው ስትቀርቡ አንተና ልጆችህ የወይን ጠጅና የሚያሰክርን ነገር ሁሉ አትጠጡ፤ ይህም ለልጅ ልጃችሁ የዘለዓለም ሥርዐት ይሆናል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዳትሞቱ ወደ መገናኛው ድንኳን ስትገቡ አንተና ልጆችህ የወይን ጠጅና የሚያሰክርን ነገር ሁሉ አትጠጡ፤ ይህም ለልጅ ልጃችሁ የዘላለም ሥርዓት ይሆናል፤ |
ከመጋረጃው ውጭ ባለው በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በምስክሩ ታቦት ፊት አሮንና ልጆቹ ከማታ እስከ ማለዳ ድረስ በጌታ ፊት ያሰናዱት፤ በእስራኤል ልጆች ዘንድ በትውልዳቸው የዘለዓለም ሥርዓት ይሁን።”
እነዚህ ደግሞ ከወይን ጠጅ የተነሣ ይስታሉ፤ ከሚያሰክርም መጠጥ የተነሣ ይንገዳገዳሉ፤ ካህኑና ነቢዩ ከሚያሰክር መጠጥ የተነሣ ይስታሉ፥ በወይን ጠጅም ይቀባዥራሉ፥ ከሚያሰክርም መጠጥ የተነሣ ይንገዳገዳሉ፤ ራእይ ሲያዩ ይስታሉ፥ በፍርድም ይሰናከላሉ።
ካህኑም እነዚህን ለመወዝወዝ ቁርባን በጌታ ፊት ይወዘውዛቸዋል፤ ይህም ከሚወዘወዘው ፍርምባና ከሚቀርበው ወርች ጋር ለካህኑ የተቀደሰ ድርሻው ነው። ከዚያም በኋላ ናዝራዊው ወይን ሊጠጣ ይችላል።
ከወይን ጠጅና ከሚያሰክር መጠጥ ራሱን ይለይ፤ ከወይን ወይም ከሚያሰክር መጠጥ የሚሠራን ሆምጣጤ አይጠጣ፥ ማንኛውንም ዓይነት የወይን ዘለላ ጭማቂ አይጠጣ፤ የወይን ዘለላ ወይም ዘቢብ አይብላ።
ኤጲስ ቆጶስ እንደ እግዚአብሔር መጋቢ ነቀፋ የሌለበት ሊሆን ይገባዋል፤ የማይኮራ፥ የማይቆጣ፥ የማይሰክር፥ ጠበኛ ያልሆነ፥ ለገንዘብ የማይስገበገብ፥