La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሰቈቃወ 4:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሔት። ፊታቸው ከጥቀርሻ ይልቅ ጠቁሮአል፥ በመንገድም አልታወቁም፥ ቁርበታቸው ወደ አጥንታቸው ተጣብቆአል፥ ደርቆአል፥ እንደ እንጨት ሆኖአል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አሁን ግን ከጥላሸት ይልቅ ጠቍረዋል፤ በመንገድም የሚያውቃቸው የለም፤ ቈዳቸው ከዐጥንታቸው ጋራ ተጣብቋል፤ እንደ ዕንጨትም ደርቀዋል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አሁን ግን ፊታቸው እንደ ጥላሸት ስለ ጠቈረ፥ በየመንገዱ ወድቀው ሲገኙ የሚያውቃቸው የለም፤ እንደ እንጨት የደረቀ ቆዳቸው በአጥንታቸው ላይ ተጣብቆአል።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሔት። ፊታ​ቸው ከጥ​ቀ​ርሻ ይልቅ ጠቍ​ሮ​አል፤ በመ​ን​ገ​ድም አል​ታ​ወ​ቁም፤ ቍር​በ​ታ​ቸው ወደ አጥ​ን​ታ​ቸው ተጣ​ብ​ቆ​አል፤ ደር​ቆ​አል፤ እንደ እን​ጨ​ትም ሆኖ​አል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሔት። ፊታቸው ከጥቀርሻ ይልቅ ጠቍሮአል፥ በመንገድም አልታወቁም፥ ቁርበታቸው ወደ አጥንታቸው ተጣብቆአል፥ ደርቆአል፥ እንደ እንጨት ሆኖአል።

Ver Capítulo



ሰቈቃወ 4:8
17 Referencias Cruzadas  

አጥንቴ ከቁርበቴና ከሥጋዬ ጋር ተጣበቀ፥ ድድ ብቻ ቀርቶልኝ አመለጥሁ።


ከሩቅም ሆነው ዓይናቸውን ባነሡ ጊዜ አላወቁትም፤ ድምፃቸውንም አሰምተው አለቀሱ፥ እያንዳንዳቸውም መጐናጸፊያቸውን ቀደዱ፥ ወደ ላይም ወደ ራሳቸው ላይ ትቢያ ነሰነሱ።


ቆዳዬ ጠቈረ፥ ከእኔም ተለይቶ እርግፍግፍ አለ፥ አጥንቴም ከትኩሳት የተነሣ ተቃጠለ።


ሥጋው እስከማይታይ ድረስ ይሰለስላል፥ ተሸፍኖ የነበረውም አጥንት ይገለጣል።


ከቁጣህና ከመዓትህም የተነሣ፥ አንሥተኸኛልና፥ ጥለኸኝማልና።


በጢስ ውስጥ እንዳለ አቁማዳ ሆኛለሁና፥ ሥርዓትህን ግን አልረሳሁም።


በቀንና በሌሊት እጅህ ከብዳብኛለችና፥ ጉልበቴ በበጋ ትኩሳት ዛለ።


ፍላጾችህ ወግተውኛልና፥ እጅህንም በላዬ ላይ አክብደህብኛልና።


ፊቱ ከሰዎች ሁሉ ይልቅ፥ መልኩም ከሰዎች ልጆች ይልቅ ተጐሳቁሎአልና ብዙ ሰዎች ስለ አንተ እንደ ተደነቁ፥ እንዲሁ ብዙ አሕዛብን ያስደንቃል፤


ከሚያቃጥል ከራብ ትኩሳት የተነሣ ቁርበታችን እንደ ምድጃ ጠቈረ።


ከፊታቸው አሕዛብ ይንቀጠቀጣሉ፥ የሰውም ፊት ሁሉ ይጠቁራል።


ብሩን በዝብዙ፥ ወርቁንም በዝብዙ፤ ሃብቷ ማለቂያ የለውምና፥ የከበረው የዕቃዋ ሁሉ ብዛት አይቆጠርምና።


‘ከከተማችሁም በእግሮቻችን ላይ የተጣበቀብንን ትቢያ ሳይቀር እናንተን በመቃወም እናራግፋለን፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር መንግሥት ቀርቦአል፥ ይህን እወቁ።’