እርሱም ቤተ መቅደሱን፥ ቤተ መንግሥቱን፥ በኢየሩሳሌም የሚኖሩ የታላላቅ ሰዎችን ቤቶችና በከተማው ውስጥ የሚገኙትንም ሌሎች ቤቶች ሁሉ በእሳት አቃጠለ፤
ሰቈቃወ 2:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሄ። ጌታ እንደ ጠላት ሆነ፥ እስራኤልን ዋጠ፥ አዳራሾችዋን ሁሉ ዋጠ፥ አምቦችዋን አጠፋ፥ በይሁዳም ሴት ልጅ ኀዘንና ልቅሶ አበዛ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጌታ እንደ ጠላት ሆነ፤ እስራኤልንም ዋጠ፤ ቤተ መንግሥቶቿን ሁሉ ዋጠ፤ ምሽጎቿን አፈራረሰ፤ በይሁዳ ሴት ልጅ፣ ልቅሶንና ሰቈቃን አበዛ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንደ ጠላት እስራኤልን አጠፋ፤ ቤተ መንግሥቶችዋን አወደመ፤ ምሽጎችዋን አፈራረሰ፤ በይሁዳ ሕዝብም ለቅሶና ዋይታን አበዛ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሄ። እግዚአብሔር እንደ ጠላት ሆነብኝ፤ እስራኤልን አሰጠመ። አዳራሾችዋን ሁሉ ዋጠ፤ አንባዎችዋንም አጠፋ። በይሁዳም ሴት ልጅ ውርደትንና ጕስቍልናን አበዛ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሄ። ጌታ እንደ ጠላት ሆነ፥ እስራኤልን ዋጠ፥ አዳራሾችዋን ሁሉ ዋጠ፥ አምቦችዋን አጠፋ፥ በይሁዳም ሴት ልጅ ኀዘንና ልቅሶ አበዛ። |
እርሱም ቤተ መቅደሱን፥ ቤተ መንግሥቱን፥ በኢየሩሳሌም የሚኖሩ የታላላቅ ሰዎችን ቤቶችና በከተማው ውስጥ የሚገኙትንም ሌሎች ቤቶች ሁሉ በእሳት አቃጠለ፤
‘የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ የባቢሎንን ንጉሥ በቅጥርም ውጭ የከበቡአችሁን ከለዳውያንን የምትወጉበትን በእጃችሁ ያለውን የጦር መሣርያ እመልሳለሁ፥ እነርሱንም ወደዚህች ከተማ ውስጥ እሰበስባቸዋለሁ።
ውሽሞችህ ሁሉ ረስተውሃል አይፈልጉህምም፤ በደልህ ታላቅ ስለሆነ ኃጢአትህም ስለ በዛ፥ ጨካኝ ሰው እንደሚቀጣው ጠላትም እንደሚያቆስለው አቁስዬሃለሁና።
ቤት። ጌታ የያዕቆብን ማደሪያዎች ሁሉ ዋጠ፥ አልራራምም፥ በመዓቱ የይሁዳን ሴት ልጅ አምቦች አፈረሰ፥ ወደ ምድርም አወረዳቸው መንግሥቱንና አለቆችዋን አረከሰ።
ዳሌጥ። ቀስቱን እንደ ጠላት ገተረ፥ እንደ አስጨናቂ ቀኝ እጁን አጸና፥ ለዓይንም የሚያምረውን ሁሉ ገደለ፥ በጽዮን ሴት ልጅ ድንኳን መዓቱን እንደ እሳት አፈሰሰ።