በዚህ ጊዜ የቢክሪ ልጅ ስሙ ሼባዕ የተባለ አንድ ከንቱ ብንያማዊ በዚያ ነበረ፤ እርሱም መለከት ነፍቶ እንዲህ ሲል ጮኸ፤ “እኛ ከዳዊት ድርሻ የለንም፤ ከእሴይም ልጅ ርስት የለንም፤ እስራኤል ሆይ፤ እያንዳንድህ ወደ ድንኳንህ ተመለስ!”
መሳፍንት 20:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሁንም እነርሱን ገድለን ይህን ክፉ ድርጊት ከእስራኤል እንድናስወግድ፥ እነዚያን የጊብዓን ነውረኞች አሳልፋችሁ ስጡን።” ብንያማውያን ግን ወገኖቻቸውን እስራኤላውያንን አልሰሟቸውም ነበር፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሁንም እነርሱን ገድለን ይህን ክፉ ድርጊት ከእስራኤል እንድናስወግድ፣ እነዚያን የጊብዓን ምናምንቴ ሰዎች አሳልፋችሁ ስጡን።” ብንያማውያን ግን ወገኖቻቸውን እስራኤላውያንን አልሰሟቸውም ነበር፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱን ገድለን ይህን ክፉ ነገር ከእስራኤል እናስወግድ ዘንድ እነዚያን በጊብዓ ያሉትን ነውረኞች አሳልፋችሁ ስጡን።” የብንያም ሕዝብ ግን የቀሩት እስራኤላውያን የነገሩአቸውን ነገር አልተቀበሉም፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አሁንም በገባዖን ውስጥ የበደሉ የዐመፅ ሰዎችን እንድንገድላቸው አውጥታችሁ ስጡን፤ ከእስራኤልም ልጆች ክፋትን እናርቃለን።” የብንያም ልጆች ግን የወንድሞቻቸውን የእስራኤልን ልጆች ቃል ሊሰሙ አልወደዱም። |
በዚህ ጊዜ የቢክሪ ልጅ ስሙ ሼባዕ የተባለ አንድ ከንቱ ብንያማዊ በዚያ ነበረ፤ እርሱም መለከት ነፍቶ እንዲህ ሲል ጮኸ፤ “እኛ ከዳዊት ድርሻ የለንም፤ ከእሴይም ልጅ ርስት የለንም፤ እስራኤል ሆይ፤ እያንዳንድህ ወደ ድንኳንህ ተመለስ!”
እነሆም፥ ነቢይ ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ አክዓብ ቀርቦ፦ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘ይህን ብዙ ጭፍራ ሁሉ ታያለህን? እነሆ፥ ዛሬ በእጅህ አሳልፌ እሰጠዋለሁ፥ እኔም እግዚአብሔር እንደሆንሁ ታውቃለህ’ አለ።”
ክፉዎች ሰዎችና ምናምንቴዎችም ወደ እርሱ ተሰበሰቡ፤ ሮብዓም ሕፃንና ለጋ በነበረበት ጊዜ፥ ሊቋቋማቸውም ባልቻለበት ጊዜ፥ በሰሎሞን ልጅ በሮብዓም ላይ በረቱበት።
እርሱም እየተናረ ሳለ ንጉሡ እንዲህ አለው፦ “በውኑ አንተ የንጉሡ አማካሪ ልትሆን ሾመነሃልን? ተው፤ እንዲገድሉህ ለምን ትሻለህ?” ነቢዩም፦ “ይህን አድርገሃልና፥ ምክሬንም አልሰማህምና ጌታ ሊያጠፋህ እንዳሰበ አወቅሁ” ብሎ ተወ።
“እነዚህን ነገሮች የሚያደርጉ ሞት ይገባቸዋል” የሚለውን ትክክለኛውን የእግዚአብሔርን ሕግ ቢያውቁም፥ እነዚህን ነገሮች ማድረግ ብቻ ሳይሆን፥ እንዲህ የሚያደርጉትንም ያበረታታሉ።
ከግብጽ ባወጣችሁና ከባርነት ምድር በዋጃችሁ በአምላካችሁ በጌታ ላይ ሊያስታችሁ ተናግሮአልና፥ አምላካችሁ ጌታ እንድትከተሉት ካዘዛችሁ መንገድ እንድትመለሱ አድርጎአልና፥ ያ ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ይገደል፤ ስለዚህ ክፉውን ከመካከላችሁ አስወግዱ።”
“የአባትህ፥ ወይም የእናትህ ልጅ ወንድምህ፥ ወንድ ልጅህ፥ ወይም ሴት ልጅህ ወይም የምትወዳት ሚስትህ ወይም የቅርብ ወዳጅህ አንዳቸው ቢሆኑ በምሥጢር ሊያስትህ ቢሞክር፥
አምላክህን ጌታን ለማገልገል በዚያ የሚቆመውን ካህኑን ወይም ፈራጁን ባለመታዘዝ የሚዳፈር፥ ያ ሰው ይሙት፥ ከእስራኤልም መካከል ክፋትን አስወግድ፥
ከዚያም በኋላ የከተማዪቱ ሰዎች ሁሉ እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ይውገሩት፤ ክፉውንም ከመካከልህ አስወግድ፤ እስራኤልም ሁሉ ይህን ሰምቶ ይፈራል።
ብላቴናይቱን ወደ አባትዋ ቤት ደጅ ያውጡአት፥ በእስራኤልም ዘንድ የማይገባውን ነገር አድርጋለችና፥ በአባትዋም ቤት አመንዝራለችና የከተማዋ ሰዎች እስክትሞት ድረስ በድንጋይ ይውገሩአት፥ ይህን በማድረግም ክፉውን ነገር ከመካከላችሁ አስወግዱ።
ሁለቱን ወደዚያች ከተማ በር አውጡአቸው፥ ብላቴናይቱ በከተማ ውስጥ ሳለች አልጮኸችምና፥ ሰውዬውም የባልንጀራውን ሚስት አስነውሮአልና እስኪሞቱ ድረስ በድንጋይ ውገሩአቸው፥ በዚህም ዓይነት ይህን ክፉ ነገር ከመካከላችሁ አስወግዱ።
“አንድ ሰው ከእስራኤላውያን ወንድሞቹ አንዱን ፈንግሎ በመውሰድ ባርያ ሲያደርገው ወይም ሲሸጠው ቢገኝ፥ ፈንጋዩ ይሙት። በዚህ ዓይነት ክፉውን ነገር ከመካከልህ ታስወግዳለህ።
በግብዣው ላይ እየተደሰቱ ሳለ፥ ጥቂት የከተማይቱ ወስላቶች ቤቱን ከበቡ፤ በሩንም እየደበደቡ፥ “ዝሙት እንድንፈጽም በት ቤትህ የገባውን ሰው አውጣው” በማለት የቤቱ ባለቤት በሆነው ሽማግሌ ላይ ጮኹበት።
ሰውስ በሰው ቢበድል እግዚአብሔር ይታደገዋል፤ ሰው ግን ጌታን ቢበድል ስለ እርሱ የሚለምን ማን ነው?” እነርሱ ግን ጌታ ሊገድላቸው ወድዷልና የአባታቸውን ቃል አልሰሙም።
ከዳዊት ተከታዮች ክፉዎቹና ምግባረ ቢሶቹ ግን፥ “አብረውን ስላልዘመቱ ካመጣነው ምርኮ አናካፍላቸውም፤ እያንዳንዱ ሚስቱንና ልጆቹን ብቻ ይዞ መሄድ ይችላል” አሉ።