Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 13:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ክፉዎች ሰዎችና ምናምንቴዎችም ወደ እርሱ ተሰበሰቡ፤ ሮብዓም ሕፃንና ለጋ በነበረበት ጊዜ፥ ሊቋቋማቸውም ባልቻለበት ጊዜ፥ በሰሎሞን ልጅ በሮብዓም ላይ በረቱበት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 የሰሎሞን ልጅ ሮብዓም ገና ሕፃን ሳለ፣ ምንም ማድረግ በማይችልበትና እነርሱንም ለመቋቋም ዐቅሙ በማይፈቅድለት ጊዜ የማይረቡ ምናምንቴዎች በዙሪያው ተሰበሰቡበት፣ በረቱበትም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ዘግየት ብሎም ኢዮርብዓም የማይረቡ ወሮበሎችን ሰበሰበ፤ እነርሱም በዕድሜው ማነስና በዕውቀት ያልበሰለ በመሆኑ ሊቋቋማቸው የማይችለውን የሰሎሞንን ልጅ ሮብዓምን በረቱበት።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ክፉ​ዎች ሰዎ​ችና የሕግ ተላ​ላ​ፊ​ዎች ልጆ​ችም ወደ እርሱ ተሰ​በ​ሰቡ፤ ሮብ​ዓም ሕፃን በነ​በ​ረና በልቡ ድፍ​ረት ባል​ነ​በ​ረው ጊዜ፥ ሊቋ​ቋ​መ​ውም ባል​ቻ​ለ​በት ጊዜ፥ በሰ​ሎ​ሞን ልጅ በሮ​ብ​ዓም ላይ በረ​ታ​በት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ክፉዎች ሰዎችና ምናምንቴዎችም ወደ እርሱ ተሰበሰቡ፤ ሮብዓም ሕፃንና ለጋ በነበረበት ጊዜ፥ ሊቋቋማቸውም ባልቻለበት ጊዜ፥ በሰሎሞን ልጅ በሮብዓም ላይ በረቱበት።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 13:7
20 Referencias Cruzadas  

ምንም እንኳ ዛሬ የተቀባሁ ንጉሥ ብሆንም፥ እኔ ደካማ ሰው ነኝ፤ እነዚህ የጽሩያ ልጆች እጅግ በርትተውብኛል። ጌታ ለክፉ አድራጊ የእጁን ይስጠው።”


የአዴርም ልጅ፦ “ለሚከተለኝ ሕዝብ የሰማርያ ትቢያ ጭብጥ ጭብጥ ይበቃው እንደሆነ፥ አማልክት ይህን ያድርጉብኝ ይህንም ይጨምሩብኝ” ብሎ ላከበት።


እነሆም፥ ነቢይ ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ አክዓብ ቀርቦ፦ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘ይህን ብዙ ጭፍራ ሁሉ ታያለህን? እነሆ፥ ዛሬ በእጅህ አሳልፌ እሰጠዋለሁ፥ እኔም እግዚአብሔር እንደሆንሁ ታውቃለህ’ አለ።”


እስራኤልም ሁሉ ንጉሡ እንዳልሰማቸው ባዩ ጊዜ ሕዝቡ ለንጉሡ እንዲህ ብለው መለሱለት፦ “በዳዊት ዘንድ ምን ድርሻ አለን? በእሴይም ልጅ ዘንድ ርስት የለንም፤ እስራኤል ሆይ! ወደ እየድንኳኖቻችሁ ተመለሱ፤ ዳዊት ሆይ! አሁን ቤትህን ተመልከት።” እስራኤልም ሁሉ ወደ እየድንኳኖቻቸው ሄዱ።


ንጉሡም ሮብዓም በኢየሩሳሌም በረታ ንጉሥም ሆነ፤ ሮብዓምም በነገሠ ጊዜ የአርባ አንድ ዓመት ጐልማሳ ነበረ፤ ጌታም ስሙን እንዲያኖርባት ከእስራኤል አገር ሁሉ በመረጣት ከተማ በኢየሩሳሌም ዐሥራ ሰባት ዓመት ነገሠ፤ እናቱም የአሞን ሴት ናዕማ ነበረች።


የአላዋቂና የነውረኞች ልጆች ናቸው፥ ከምድርም በግርፋት የተባረሩ ናቸው።”


ከአታላዮች ጋር አልተቀመጥሁም፥ ከአስመሳዮችም ጋር አልገባሁም።


መሬቱን የሚቆፍር ሰው እንጀራ ይጠግባል፥ ለከንቱ ነገር የሚሮጥ ግን ማስተዋል የተሣነው ነው።


ምድሩን የሚያርስ እንጀራ ይጠግባል፥ የማይረቡ ሰዎችን የሚከተል ግን ድህነት ይሞላበታል።


ንጉሥሽ ሕፃን የሆነ፥ መኳንንቶችሽም ማልደው የሚበሉ፥ አንቺ አገር ሆይ፥ ወዮልሽ!


ልጆችን መሪዎቻቸው አደርጋለሁ፤ ያልበሰሉ ሕፃናትም ይገዟቸዋል።


አይሁድ ግን ቀንተው ከሥራ ፈቶች ክፉ ሰዎችን አመጡ ሕዝብንም ሰብስበው ከተማውን አወኩ፤ ወደ ሕዝብም ያወጡአቸው ዘንድ ፈልገው ወደ ኢያሶን ቤት ቀረቡ፤


ወንድሞች ሆይ፤ በአስተሳሰባችሁ ሕፃናት አትሁኑ፤ ለክፉ ነገር ሕፃናት ሁኑ እንጂ በአስተሳሰባችሁ ግን ጐልማሶች ሁኑ።


ክፉ ሰዎች ከመካከላችሁ ተነሥተው አንተ የማታውቃቸውን፥ ‘ሌሎች አማልክትን ሄደን እናምልክ’ በማለት የከተማቸውን ሕዝብ እያሳቱ ቢሆን፥


የማይታዘዙና ከንቱ ነገርን የሚያወሩ የሚያታልሉ በተለይም ከተገረዙት ወገን የሆኑ ብዙ ሰዎች አሉና፤


እስከ አሁን በነበረው ጊዜ አስተማሪዎች ልትሆኑ ሲገባችሁ፥ እንደገና የእግዚአብሔር ቃላት የመጀመሪያውን ትምህርት እንዲያስተምራችሁ ሰው ያስፈልጋችኋልና፤ የሚያስፈልጋችሁም ወተት ነው እንጂ ጠንካራ ምግብ አይደለም።


ስለዚህም ዮፍታሔ ከወንድሞቹ ሸሽቶ መኖሪያውን ጦብ በተባለች ምድር አደረገ፤ እዚያም ወሮበሎች ተሰባስበው ተከተሉት።


እነርሱም በኣልብሪት ቤተ ጣዖት ሰባ ሰቅል ናስ ሰጡት፤ አቤሜሌክም በዚያ ወሮበሎችንና ምናምንቴዎችን ቀጠረበት፤ እነርሱም ተከተሉት።


የተጨነቁ፥ ዕዳ ያለባቸውና የተከፉ ወደ እርሱ ተሰባሰቡ፤ እርሱም መሪያቸውም ሆነ። እነርሱም አራት መቶ ያህል ሰዎች ነበሩ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos