Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ቆሮንቶስ 6:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ክርስቶስስ ከቤልሆር ጋር ምን ስምምነት አለው? ወይስ የሚያምን ከማያምን ጋር ምን ክፍል አለው?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ክርስቶስ ከቤልሆር ጋራ ምን ስምምነት አለው? የሚያምን ከማያምን ጋራ ምን ኅብረት አለው?

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ክርስቶስና ዲያብሎስ እንዴት ሊስማሙ ይችላሉ? የሚያምንና የማያምንስ በምን ሊወዳጁ ይችላሉ?

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ክር​ስ​ቶ​ስን ከቤ​ል​ሆር ጋር አንድ የሚ​ያ​ደ​ር​ገው ማን ነው? ወይስ ምእ​መ​ና​ንን ከመ​ና​ፍ​ቃን ጋር አንድ ወገን የሚ​ያ​ደ​ር​ጋ​ቸው ማን ነው?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ክርስቶስስ ከቤልሆር ጋር ምን መስማማት አለው? ወይስ የሚያምን ከማያምን ጋር ምን ክፍል አለው?

Ver Capítulo Copiar




2 ቆሮንቶስ 6:15
14 Referencias Cruzadas  

ኤልያስም ወጥቶ ለሰዎቹ፦ “እስከ መቼ ድረስ በሁለት ልብ ስታወላውሉ ትኖራላችሁ? እንግዲህ ጌታ እውነተኛ አምላክ ከሆነ እርሱን አምልኩ! ወይም ባዓል እውነተኛ አምላክ ከሆነ እርሱኑ አምልኩ!” አላቸው፤ ሕዝቡ ግን አንዲት ቃል እንኳ አልመለሱም።


ማንም ቢሆን ግን ለገዛ ዘመዶቹ በተለይም ለቤተ ሰቡ አባላት የማያስብ ከሆነ፥ እምነትን የካደና ከማያምን ሰው ይልቅ የባሰ ነው።


ጴጥሮስ ግን እንዲህ አለው “የእግዚአብሔርን ስጦታ በገንዘብ እንድታገኝ አስበሃልና ብርህ ከአንተ ጋር ይጥፋ።


ሕዝቡ ግን ያከብሩአቸው ነበር፤ የሚያምኑትም ከፊት ይልቅ ለጌታ ይጨመሩለት ነበር፤ ወንዶችና ሴቶችም ብዙ ነበሩ።


ያመነና የተጠመቀ ይድናል፤ ያላመነ ግን ይፈረድበታል።


ዘሩባቤል፥ ኢያሱና የቀሩትም የእስራኤል አባቶች አለቆች፦ “የአምላካችንን ቤት ማነፅ ለእኛና ለእናንተ አይደለም፥ እኛ ለብቻችን ሆነን ንጉሥ ቂሮስ የፋርስ ንጉሥ እንዳዘዘን ለጌታ ለእስራኤል አምላክ ቤት እንገነባለን” አሉአቸው።


በግብዣው ላይ እየተደሰቱ ሳለ፥ ጥቂት የከተማይቱ ወስላቶች ቤቱን ከበቡ፤ በሩንም እየደበደቡ፥ “ዝሙት እንድንፈጽም በት ቤትህ የገባውን ሰው አውጣው” በማለት የቤቱ ባለቤት በሆነው ሽማግሌ ላይ ጮኹበት።


አሁንም እነርሱን ገድለን ይህን ክፉ ድርጊት ከእስራኤል እንድናስወግድ፥ እነዚያን የጊብዓን ነውረኞች አሳልፋችሁ ስጡን።” ብንያማውያን ግን ወገኖቻቸውን እስራኤላውያንን አልሰሟቸውም ነበር፤


የዔሊም ልጆች ለጌታ ክብር የማይሰጡ ስድ አደጎች ነበሩ።


ነገር ግን ወንድም ወንድሙን ይከሳል፤ ይህም በማያምኑ ፊት ይደረጋል!


እምነታችሁና ተስፋችሁ በእግዚአብሔር ይሆን ዘንድ፥ ከሞት ባስነሣው ክብርንም በሰጠው፥ በእግዚአብሔር በእርሱ ትተማመናላችሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios