መሳፍንት 15:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እጅግ ተጠምቶ ስለ ነበር፤ “እነሆ፤ ለአገልጋይህ ይህን ታላቅ ድል አጐናጽፈሃል፤ ታዲያ አሁን በውሃ ጥም ልሙት? እንዴትስ በእነዚህ ባልተገረዙ ፍልስጥኤማውያን እጅ ልውደቅ?” በማለት ወደ ጌታ ጮኸ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እጅግ ተጠምቶ ስለ ነበር፤ “እነሆ፤ ለአገልጋይህ ይህን ታላቅ ድል አጐናጽፈሃል፤ ታዲያ አሁን በውሃ ጥም ልሙት? እንዴትስ በእነዚህ ባልተገረዙ ፍልስጥኤማውያን እጅ ልውደቅ?” በማለት ወደ እግዚአብሔር ጮኸ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ሶምሶን በጣም ተጠማ፤ ወደ እግዚአብሔርም እንዲህ ብሎ ጮኸ፤ “ይህን ትልቅ ድል ለአገልጋይህ ሰጥተኸኛል፤ ታዲያ፥ እኔ አሁን በውሃ ጥም ልሙትን? ባልተገረዙ ሰዎች እጅም ልውደቅን?” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም እጅግ ተጠምቶ ነበርና፥ “አንተ ይህችን ታላቅ ማዳን በባሪያህ እጅ ሰጥተሃል፤ አሁንም በጥም እሞታለሁ፤ ባልተገረዙትም እጅ እወድቃለሁ” ብሎ ወደ እግዚአብሔር ጮኸ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም እጅግ ተጠምቶ ነበርና፦ አንተ ይህችን ታላቅ ማዳን በባሪያህ እጅ ሰጥተሃል፥ አሁንም በጥም እሞታለሁ፥ ባልተገረዙትም እጅ እወድቃለሁ ብሎ ወደ እግዚአብሔር ጮኸ። |
ከዚህ በላይ ምን ልበል? ስለ ጌዴዎን፥ ስለ ባርቅ፥ ስለ ሳምሶን፥ ስለ ዮፍታሔ፥ ስለ ዳዊት፥ ስለ ሳሙኤልና ስለ ነቢያት እንዳልተርክ ጊዜ ያጥርብኛል።
አባቱና እናቱም፥ “ከዘመዶችህ ወይም ከሕዝባችን ሁሉ መካከል ለአንተ የምትሆን ሴት መች ታጣችና ነው ወዳልተገረዙት አሕዛብ ዘንድ ሚስት ፍለጋ የሄድከው?” አሉት። ሳምሶንም አባቱን፥ “ልቤን የማረከችው እርሷ ናትና እርሷን አጋባኝ” አለው።
ሳምሶንም ወደ ጌታ እንዲህ ሲል ጸለየ፤ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ አስበኝ፤ አምላክ ሆይ፤ እባክህን አንድ ጊዜ ብቻ ብርታት ስጠኝና ስለ ጠፉት ዐይኖቼ ፍልስጥኤማውያንን አንዴ ልበቀላቸው።”
ዳዊት በአጠገቡ የቆሙትን ሰዎች፥ “ይህን ፍልስጥኤማዊ ገድሎ እንዲህ ያለውን ውርደት ከእስራኤል ለሚያስወግድ ሰው ምን ይደረግለታል? ደግሞስ የሕያው እግዚአብሔርን ሠራዊት ይገዳደር ዘንድ ይህ ያልተገረዘ ፍልስጥኤማዊ እርሱ ማነው?” ሲል ጠየቀ።
ባርያህ አንበሳውንም ድቡንም ገድሏል፤ ይህም ያልተገረዘ ፍልስጥኤማዊ የሕያው እግዚአብሔርን ሠራዊት ተገዳድሯልና መጨረሻው ከእነርሱ እንደ አንዱ ይሆናል።
ዳዊት በልቡ፦ “ከእነዚህ ቀናት በአንዱ በሳኦል እጅ መገደሌ ስለማይቀር፥ የሚበጀኝ ወደ ፍልስጥኤማውያን ምድር መሸሽ ብቻ ነው፤ ከዚያ በኋላም ሳኦል በእስራኤል ሁሉ እኔን ማሳደዱን ይተዋል፤ እኔም ከእጁ አመልጣለሁ” ብሎ አሰበ።