Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መሳፍንት 15:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 እር​ሱም እጅግ ተጠ​ምቶ ነበ​ርና፥ “አንተ ይህ​ችን ታላቅ ማዳን በባ​ሪ​ያህ እጅ ሰጥ​ተ​ሃል፤ አሁ​ንም በጥም እሞ​ታ​ለሁ፤ ባል​ተ​ገ​ረ​ዙ​ትም እጅ እወ​ድ​ቃ​ለሁ” ብሎ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኸ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 እጅግ ተጠምቶ ስለ ነበር፤ “እነሆ፤ ለአገልጋይህ ይህን ታላቅ ድል አጐናጽፈሃል፤ ታዲያ አሁን በውሃ ጥም ልሙት? እንዴትስ በእነዚህ ባልተገረዙ ፍልስጥኤማውያን እጅ ልውደቅ?” በማለት ወደ እግዚአብሔር ጮኸ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 እጅግ ተጠምቶ ስለ ነበር፤ “እነሆ፤ ለአገልጋይህ ይህን ታላቅ ድል አጐናጽፈሃል፤ ታዲያ አሁን በውሃ ጥም ልሙት? እንዴትስ በእነዚህ ባልተገረዙ ፍልስጥኤማውያን እጅ ልውደቅ?” በማለት ወደ ጌታ ጮኸ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ከዚህ በኋላ ሶምሶን በጣም ተጠማ፤ ወደ እግዚአብሔርም እንዲህ ብሎ ጮኸ፤ “ይህን ትልቅ ድል ለአገልጋይህ ሰጥተኸኛል፤ ታዲያ፥ እኔ አሁን በውሃ ጥም ልሙትን? ባልተገረዙ ሰዎች እጅም ልውደቅን?”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 እርሱም እጅግ ተጠምቶ ነበርና፦ አንተ ይህችን ታላቅ ማዳን በባሪያህ እጅ ሰጥተሃል፥ አሁንም በጥም እሞታለሁ፥ ባልተገረዙትም እጅ እወድቃለሁ ብሎ ወደ እግዚአብሔር ጮኸ።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 15:18
19 Referencias Cruzadas  

አብ​ር​ሃ​ምም አለ፥ “ምን​አ​ል​ባት በዚህ ስፍራ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራት ስለ​ሌለ በሚ​ስቴ ምክ​ን​ያት ይገ​ድ​ሉ​ኛል ብዬ ነው።


ራእየ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም በተወ ጊዜ ፀሐይ ወጣ​ች​በት። እር​ሱም በጭኑ ምክ​ን​ያት ያነ​ክስ ነበር።


የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሴቶች ልጆች ደስ እን​ዳ​ይ​ላ​ቸው፥ የቈ​ላ​ፋ​ንም ሴቶች ልጆች እልል እን​ዳ​ይሉ፥ በጌት ውስጥ አታ​ውሩ፤ በአ​ስ​ቀ​ሎ​ናም አደ​ባ​ባይ የም​ስ​ራች አት​በሉ።


ከዚ​ህም በኋላ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ሁሉ እንደ ተፈ​ጸመ ባየ ጊዜ የመ​ጽ​ሐፉ ቃል ይፈ​ጸም ዘንድ “ተጠ​ማሁ” አለ።


እን​ግ​ዲህ ምን እላ​ለሁ? ስለ ጌዴ​ዎን፥ ስለ ባርቅ፥ ስለ ሶም​ሶን፥ ስለ ዮፍ​ታሔ፥ ስለ ዳዊት፥ ስለ ሳሙ​ኤ​ልና ስለ ሌሎች ነቢ​ያት እነ​ግ​ራ​ችሁ ዘንድ ጊዜዬ አጭር ነውና።


አባ​ቱና እና​ቱም፥ “ካል​ተ​ገ​ረ​ዙት ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሚስት ለማ​ግ​ባት ትሄድ ዘንድ ከወ​ን​ድ​ሞ​ችህ ሴቶች ልጆች፥ ከሕ​ዝ​ቤም ሁሉ መካ​ከል ሴት የለ​ች​ምን?” አሉት። ሶም​ሶ​ንም አባ​ቱን፥ “ለዐ​ይኔ እጅግ ደስ አሰ​ኝ​ታ​ኛ​ለ​ችና እር​ስ​ዋን አጋ​ባኝ” አለው።


መና​ገ​ሩ​ንም በፈ​ጸመ ጊዜ መን​ጋ​ጋ​ውን ከእጁ ጣለ፤ የዚ​ያ​ንም ስፍራ ስም “ቀትለ አጽመ መን​ሰክ” ብሎ ጠራው።


ሶም​ሶ​ንም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኸ፥ እን​ዲ​ህም አለ፥ “አቤቱ ጌታዬ ሆይ! አስ​በኝ፤ ጌታዬ ሆይ! አንድ ጊዜ አበ​ር​ታኝ፤ እን​ግ​ዲህ ስለ ሁለቱ ዐይ​ኖቼ ፋንታ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን አን​ዲት በቀ​ልን እበ​ቀ​ላ​ለሁ።”


ጌዴ​ዎ​ንም ወደ ዮር​ዳ​ኖስ መጥቶ ተሻ​ገረ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ያሉት ሦስት መቶ ሰዎች ተሻ​ገሩ፤ ምንም እንኳ ቢራ​ቡም ያሳ​ድዱ ነበር።


ዳዊ​ትም በአ​ጠ​ገቡ ለቆ​ሙት ሰዎች፦ ይህን ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማዊ ለሚ​ገ​ድል፥ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ተግ​ዳ​ሮ​ትን ለሚ​ያ​ርቅ ሰው በውኑ ይህ ይደ​ረ​ግ​ለ​ታል? የሕ​ያው አም​ላ​ክን ጭፍ​ሮች የሚ​ገ​ዳ​ደር ይህ ያል​ተ​ገ​ረዘ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማዊ ማን ነው?” ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው።


እኔ ባሪ​ያህ አን​በ​ሳና ድብ ገደ​ልሁ፤ ይህም ያል​ተ​ገ​ረ​ዘው ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማዊ ከእ​ነ​ርሱ እንደ አንዱ ይሆ​ናል። እን​ግ​ዲህ እገ​ድ​ለው ዘንድ፥ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ተግ​ዳ​ሮ​ትን አስ​ወ​ግድ ዘንድ ዛሬ አል​ሄ​ድ​ምን? የሕ​ያው አም​ላክ ጭፍ​ሮ​ችን ይገ​ዳ​ደር ዘንድ ይህ ቈላፍ ምን​ድን ነው?”


ዳዊ​ትም በልቡ፥ “አንድ ቀን በሳ​ኦል እጅ እሞ​ታ​ለሁ፤ ወደ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ምድር ከመ​ሸሸ በቀር የሚ​ሻ​ለኝ የለም፤ ሳኦ​ልም በእ​ስ​ራ​ኤል አው​ራጃ ሁሉ እኔን መሻት ይተ​ዋል፤ እን​ዲ​ሁም ከእጁ እድ​ና​ለሁ” አለ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos