መሳፍንት 1:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢያሱ ከሞተ በኋላ የእስራኤል ሕዝብ “ከነዓናውያንን ለመውጋት ማን በቅድሚያ ይወጣልናል?” ብለው ጌታን ጠየቁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢያሱ ከሞተ በኋላ እስራኤላውያን፣ “ከነዓናውያንን ለመውጋት ማን ቀድሞ ይውጣልን?” ብለው እግዚአብሔርን ጠየቁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢያሱ ከሞተ በኋላ የእስራኤል ሕዝብ “በከነዓናውያን ላይ አደጋ ለመጣል ከነገዶቻችን መካከል ተቀዳሚ ሆኖ ማን ይዝመት?” ሲሉ እግዚአብሔርን ጠየቁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም ሆነ፤ ኢያሱ ከሞተ በኋላ የእስራኤል ልጆች፥ “ከነዓናውያንን የሚወጋልን ማን አለቃ ይወጣልናል?” ብለው ወደ እግዚአብሔር ጠየቁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም ሆነ፥ ኢያሱ ከሞተ በኋላ የእስራኤል ልጆች፦ ከነዓናውያንን ለመውጋት ማን በፊት ይወጣልናል? ብለው እግዚአብሔርን ጠየቁ። |
በፍርዱ በደረት ኪስም ውስጥ ኡሪምንና ቱሚምን ታደርጋለህ፥ በጌታ ፊት በገባ ጊዜ በአሮን ልብ ላይ ይሆናሉ፤ አሮንም በጌታ ፊት ሁልጊዜ የእስራኤልን ልጆች ፍርድ በልቡ ላይ ይሸከማል።
በካህኑም በአልዓዛር ፊት ይቁም፤ እርሱም በጌታ ፊት በኡሪም ፍርድ ይጠይቅለት፤ እርሱ ከእርሱም ጋር የእስራኤል ልጆች ማኅበሩም ሁሉ በቃሉ ይውጡ፥ በቃሉም ይግቡ።”
የምናሴ ነገድ ግን በቤትሳን፥ በታዕናክ፥ በዶር፥ በይብለዓም፥ በመጊዶንና በየአካባቢያቸው ያሉት መንደሮች ነዋሪውን ሕዝብ ስላላስወጡ፥ ከነዓናውያን ኑሮአቸውን በዚያው ለማድረግ ወሰኑ።
እስራኤላውያን ወደ ቤቴል ወጡ፤ እግዚአብሔርንም “ብንያማውያንን ለመውጋት ከመካከላችን ማን ቀድሞ ይውጣ?” ሲሉ ጠየቁ። ጌታም፥ “ይሁዳ ቀድሞ ይውጣ” ብሎ መለሰ።
እስራኤላውያን ወጥተው እስኪመሽ ድረስ በጌታ ፊት አለቀሱ፤ “ወንድሞቻችንን ብንያማውያንን ለመውጋት እንደገና እንውጣን?” ብለው ጌታን ጠየቁ። ጌታም፥ “አዎን፤ ውጡና ውጉቸው” ብሎ መለሰላቸው።
የአሮን ልጅ፤ የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስም በፊቱ ይቆም ነበር። እስራኤላውያንም፥ “ወንድሞቻችንን ብንያማውያንን እንደገና ሄደን ጦርነት እንግጠማቸው ወይስ ይቅር?” ሲሉ ጠየቁ። ጌታም፥ “ሂዱ፤ በነገው ዕለት በእጃችሁ እሳልፌ እሰጣችኋለሁ” አላቸው።