Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መሳፍንት 20:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 እስራኤላውያን ወደ ቤቴል ወጡ፤ እግዚአብሔርንም “ብንያማውያንን ለመውጋት ከመካከላችን ማን ቀድሞ ይውጣ?” ሲሉ ጠየቁ። ጌታም፥ “ይሁዳ ቀድሞ ይውጣ” ብሎ መለሰ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 እስራኤላውያን ወደ ቤቴል ወጡ፤ እግዚአብሔርም፣ “ብንያማውያንን ለመውጋት ከመካከላችን ማን ቀድሞ ይውጣ?” ሲሉ ጠየቁ። እግዚአብሔርም፣ “ይሁዳ ቀድሞ ይውጣ” ብሎ መለሰ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 እስራኤላውያን ወደ ቤትኤል ወጥተው “በብንያማውያን ላይ መጀመሪያ አደጋ መጣል የሚገባው የትኛው ነገድ ነው?” ሲሉ እግዚአብሔርን ጠየቁ። እግዚአብሔርም “የይሁዳ ነገድ አስቀድሞ ይዝመት” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ተነ​ሥ​ተው ወደ ቤቴል ወጡ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም፥ “የብ​ን​ያ​ምን ልጆች ለመ​ው​ጋት መሪ ሆኖ ማን ይው​ጣ​ልን?” ብለው ጠየ​ቁት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ይሁዳ መሪ ይሁን” አለ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 የእስራኤልም ልጆች ተነሥተው ወደ ቤቴል ወጡ፥ እግዚአብሔርንም፦ የብንያምን ልጆች ለመውጋት አስቀድሞ ማን ይውጣልን? ብለው ጠየቁት፥ እግዚአብሔርም፦ ይሁዳ ይቅደም አለ።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 20:18
15 Referencias Cruzadas  

እስራኤላውያን ወጥተው እስኪመሽ ድረስ በጌታ ፊት አለቀሱ፤ “ወንድሞቻችንን ብንያማውያንን ለመውጋት እንደገና እንውጣን?” ብለው ጌታን ጠየቁ። ጌታም፥ “አዎን፤ ውጡና ውጉቸው” ብሎ መለሰላቸው።


በካህኑም በአልዓዛር ፊት ይቁም፤ እርሱም በጌታ ፊት በኡሪም ፍርድ ይጠይቅለት፤ እርሱ ከእርሱም ጋር የእስራኤል ልጆች ማኅበሩም ሁሉ በቃሉ ይውጡ፥ በቃሉም ይግቡ።”


ጾምን ቀድሱ፥ ጉባኤውንም አውጁ ሽምግሌዎችንና በምድር የሚኖሩትን ሁሉ ወደ አምላካችሁ ወደ ጌታ ቤት ሰብስቡ፥ ወደ ጌታም ጩኹ።


አሁንም እናንተ እስራኤላውያን ሁሉ በጉዳዩ ላይ ተወያዩበት፤ ፍርዳችሁንም ስጡ።”


ሰውየውም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “እኛ የመጣነው ከይሁዳ ቤተልሔም ርቆ ከሚገኘው ከኰረብታማው ከኤፍሬም አገር ነው፤ ከይሁዳ ቤተልሔም ነበርሁ፤ አሁን ወደ ጌታ ቤት እሄዳለሁ፤ ወደ ቤቱ የሚወስደኝ ሰው አላገኘሁም።


ስለዚህም ሚካ የሠራቸውን ጣዖታት፥ የእግዚአብሔር ቤት በሴሎ በነበረበት ጊዜ ሁሉ አቆሙ።


የእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ በሴሎ ተሰበሰቡ፥ በዚያም የመገናኛውን ድንኳን ተከሉ፤ እነርሱም የምድሪቱ ገዢዎች ሆኑ።


የእስራኤልም አለቆች ከስንቃቸው ወሰዱ፥ የጌታንም ምሪት አልጠየቁም።


ሙሴም ነገራቸውን በጌታ ፊት አቀረበ።


እስራኤላውያን፥ ብንያማውያንን ሳይጨምር፥ ሰይፍ የታጠቁ አራት መቶ ሺህ ተዋጊዎች አሰባሰቡ።


በማግሥቱ ጧት እስራኤላዋያን ነሥተው በጊብዓ አጠገብ ሰፈሩ፤


“አንተም ጉዞህን በመቀጠል በታቦር እስካለው ባሉጥ ዛፍ ድረስ ትሄዳለህ፤ እዚያም ሦስት ሰዎች፥ አንዱ ሦስት የፍየል ግልገል፥ ሌላው ሦስት ዳቦ፥ ሌላው ደግሞ የወይን ጠጅ የተሞላበት አቁማዳ ይዘው ወደ እግዚአብሔር ወደ ቤቴል ሲወጡ ያገኙሃል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios