ኢያሱ 21:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በይሁዳ ተራራማ አገር ያለችውን ቂርያት-አርባቅ የምትባለውን ከተማ በዙሪያዋም ያለውን መሰማሪያ ሰጡአቸው፤ እርሷም ኬብሮን ናት፥ ይህም አርባቅ የዔናቅ አባት ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም በተራራማው የይሁዳ ምድር ያለችውን ኬብሮን የተባለችውን ቂርያት አርባቅን በዙሪያዋ ካለው መሰማሪያ ጋራ ሰጧቸው፤ አርባቅ የዔናቅ አባት ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በይሁዳ ተራራማ አገር ያለችውን ቂርይትአርባቅ የምትባለውን ከተማ፥ በዙሪያዋ ካለው የግጦሽ መሬት ጋር ሰጡአቸው፤ እርስዋም ኬብሮን ናት፤ ይህም አርባቅ የዐናቅ አባት ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኤናቅ ልጆች ከተማ ቅርያትያርቦቅንና በዙሪያዋ ያሉ መሰማሪያዎችን ሰጡአቸው፤ ይህችውም በይሁዳ ተራራ ያለች ኬብሮን ናት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በይሁዳ ተራራማ አገር ያለችውን ቂርያትአርባቅ የምትባለውን ከተማ በዙሪያዋም ያለውን መሰምርያ ሰጡአቸው፥ እርስዋም ኬብሮን ናት፥ ይህም አርባቅ የዔናቅ አባት ነበረ። |
ያዕቆብም ወደ አባቱ ወደ ይስሐቅ ወደ መምሬ፥ አብርሃምና ይስሐቅ እንግዶች ሆነው ወደ ተቀመጡባት፥ ወደ ቂርያት-አርባ፥ እርሷም ኬብሮን ወደምትባለው መጣ።
የይሁዳ ሰዎች በኬብሮን በሚኖሩ ከነዓናውያን ላይ ዘመቱ፤ ኬብሮን ቀደም ሲል ቂርያት-አርባዕ ተብላ ትጠራ ነበር፤ እነርሱም ሼሻይን፥ አሒማንንና ታልማይኖችን ድል አደረጉ።