Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢያሱ 21:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 በይሁዳ ተራራማ አገር ያለችውን ቂርይትአርባቅ የምትባለውን ከተማ፥ በዙሪያዋ ካለው የግጦሽ መሬት ጋር ሰጡአቸው፤ እርስዋም ኬብሮን ናት፤ ይህም አርባቅ የዐናቅ አባት ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 እነርሱም በተራራማው የይሁዳ ምድር ያለችውን ኬብሮን የተባለችውን ቂርያት አርባቅን በዙሪያዋ ካለው መሰማሪያ ጋራ ሰጧቸው፤ አርባቅ የዔናቅ አባት ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 በይሁዳ ተራራማ አገር ያለችውን ቂርያት-አርባቅ የምትባለውን ከተማ በዙሪያዋም ያለውን መሰማሪያ ሰጡአቸው፤ እርሷም ኬብሮን ናት፥ ይህም አርባቅ የዔናቅ አባት ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 የኤ​ናቅ ልጆች ከተማ ቅር​ያ​ት​ያ​ር​ቦ​ቅ​ንና በዙ​ሪ​ያዋ ያሉ መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዎ​ችን ሰጡ​አ​ቸው፤ ይህ​ች​ውም በይ​ሁዳ ተራራ ያለች ኬብ​ሮን ናት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 በይሁዳ ተራራማ አገር ያለችውን ቂርያትአርባቅ የምትባለውን ከተማ በዙሪያዋም ያለውን መሰምርያ ሰጡአቸው፥ እርስዋም ኬብሮን ናት፥ ይህም አርባቅ የዔናቅ አባት ነበረ።

Ver Capítulo Copiar




ኢያሱ 21:11
15 Referencias Cruzadas  

በከነዓን ምድር ባለችው “ቂርያት አርባዕ” ተብላ በምትጠራው በኬብሮን ከተማ ሞተች፤ አብርሃም በሣራ ሞት ምክንያት እጅግ አዘነ፤ አለቀሰም።


ያዕቆብ በኬብሮን አጠገብ መምሬ ወደምትባል ስፍራ ወደሚኖረው አባቱ ወደ ይስሐቅ ሄደ፤ ይህም ስፍራ አብርሃምና ይስሐቅ የኖሩበት ነው።


ከአራት ዓመት በኋላ አቤሴሎም ንጉሥ ዳዊትን እንዲህ አለው፤ “ንጉሥ ሆይ! ለእግዚአብሔር የተሳልኩትን ስእለት ለመፈጸም ወደ ኬብሮን እንድሄድ ፍቀድልኝ!


ለእርሱም የተሰጠው ድርሻ በይሁዳ ግዛት የሚገኘው ኬብሮንና በእርሱም ዙሪያ ያለውን የግጦሽ ቦታ ሁሉ ያጠቃልላል።


በዚያን ጊዜ ማርያም በተራራማው በይሁዳ አገር ወዳለችው ከተማ በፍጥነት ተነሥታ ሄደች።


የኬብሮንም ስም አስቀድሞ ቂርያት አርባዕ ነበር፤ ይህም አርባዕ ከዐናቃውያን መካከል ታላቅ ሰው ነበር። ምድሪቱም ከጦርነት ዐረፈች።


ሑምጣ፥ ኬብሮንና ጺዖር ተብለው የሚጠሩ በድምሩ ዘጠኝ ከተሞች ሲሆኑ በዙሪያቸው ያሉትን መንደሮች ያጠቃልላሉ።


የመጀመሪያው ዕጣ ለእነርሱ ስለ ወጣ ከሌዊ ነገድ የአሮን ዘሮች ለሆኑት ለቀዓት ወገኖች ተሰጠ።


ይሁን እንጂ በከተማይቱ የሚገኘው የእርሻ ቦታና በክልልዋ ውስጥ ያሉት መንደሮች አስቀድሞ ለይፉኔ ልጅ ለካሌብ ርስት ሆነው ተሰጥተዋል።


የይሁዳ ሰዎች በኬብሮን በሚኖሩ ከነዓናውያን ላይ ዘመቱ፤ ኬብሮን ቀድሞ ኪርያት አርባዕ ትባል ነበር፤ እነርሱም የሼሻይን፥ የአሒማንንና የታልማይን ጐሣዎች አሸነፉ።


በኬብሮን ከተሞች ለሚኖሩ ሁሉ ላከላቸው፤ ከዚህም በቀር እርሱና ተከታዮቹ በተዘዋወሩባቸው ስፍራዎች ሁሉ ለሚኖሩ ሰዎች ስጦታ ላከ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos