ኢያሱ 2:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህንንም ነገር ሰምተን ልባችን ቀለጠ፤ ጌታ አምላካችሁም በላይ በሰማይ በታችም በምድር እርሱ አምላክ ነውና ከእናንተ የተነሣ ከእግዲህ ወዲያ ሰው ሁሉ ሐሞተ ቢስ ሆኖአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህን በሰማን ጊዜ ልባችን ቀለጠ፤ እናንተን ከመፍራት የተነሣም ያልተሸበረ ሰው አልነበረም፤ እግዚአብሔር አምላካችሁ በላይም በሰማይ፣ በታችም በምድር እርሱ አምላክ ነውና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም ይህን ሁሉ ነገር በሰማን ጊዜ በፍርሃት ልባችን ቀለጠ፤ ወኔአችን ሁሉ ጠፋ፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር በእርግጥ የሰማይና የምድር አምላክ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህንም ነገር ሰምተን በልባችን ደነገጥን፤ አምላካችሁም እግዚአብሔር በላይ በሰማይ፥ በታችም በምድር እርሱ አምላክ ነውና ከእናንተ የተነሣ ከእኛ የአንዱም እንኳን ነፍስ አልቀረም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህንም ነገር ሰምተን ልባችን ቀለጠ፥ አምላካችሁም እግዚአብሔር በላይ በሰማይ በታችም በምድር እርሱ አምላክ ነውና ከእናንተ የተነሣ ከዚያ ወዲያ ለማንም ነፍስ አልቀረለትም። |
ከዚህም በኋላ ከተከታዮቹ ጋር ወደ እግዚአብሔር ሰው ተመልሶ መጥቶ፦ “ከእስራኤል አምላክ በቀር ሌላ አምላክ አለመኖሩን እነሆ፥ አሁን ተረዳሁ፤ ስለዚህም ጌታዬ ሆይ፥ እባክህ ይህን ስጦታ ተቀበለኝ” አለው።
እንዲህም ሆነ፦ ጠላቶቻችን ሁሉ ይህን በሰሙ ጊዜ በዙሪያችን የነበሩ አሕዛብ ሁሉ ፈሩ፥ ዓይናቸውም እያየ ብዙ ውድቀት ሆነ፥ ይህ ሥራ በአምላካችን እንደ ተከናወነ አወቁ።
ስለ ግብጽ የተነገረ ትንቢት። እነሆ፥ ጌታ በፈጣን ደመና እየበረረ ወደ ግብጽ ይመጣል፤ የግብጽም ጣዖታት በፊቱ ይርዳሉ፤ የግብጽም ልብ በውስጥዋ ይቀልጣል።
ልብ እንዲቀልጥ፥ ብዙዎች እንዲሰናከሉ ነው፤ በበሮቻቸው ሁሉ ላይ የሚገድል ሰይፍ አድርጌአለሁ፥ ወዮ! እንዲያብረቀርቅ ተወልውሎአል፥ እንዲገድልም ተጠቅልሎአል።
ወዴትስ እንወጣለን? ሕዝቡ ብዙ ነው፥ ቁመቱም ከእኛ ይረዝማል፥ ከተሞቹም ታላላቆች የተመሸጉም እስከ ሰማይም የደረሱ ናቸው፥ የዔናቅንም ልጆች ደግሞ በዚያ አየናቸው፥’ ብለው ወንድሞቻችን ልባችንን አወኩት።
ኢያሱንም እንዲህ አሉት፦ “በእውነት ጌታ አገሩን ሁሉ በእጃችን አሳልፎ ሰጥቶአል፤ ከእኛም የተነሣ በአገሩ ውስጥ ያሉ ሰዎች ሁሉ በፍርሃት ቀልጠዋል።”
እንዲህም ሆነ፤ በዮርዳኖስ ማዶ በምዕራብ በኩል የነበሩት የአሞራውያን ነገሥታት ሁሉ፥ በባሕሩም አጠገብ የነበሩ የከነዓናውያን ነግሥታት ሁሉ፥ ጌታ ከእስራኤል ልጆች ፊት የዮርዳኖስን ውኃ እስኪሻገሩት ድረስ እንዳደረቀ በሰሙ ጊዜ፥ ልባቸው ቀለጠ ከእስራኤልም ልጆች የተነሣ ከዚያ ወዲያ ሐሞተ ቢስ ሆኑ።
የጋይም ሰዎች ከእነርሱ ሠላሳ ስድስት ያህል ሰዎችን ገደሉ፤ ከበሩ እስከ ሸባሪም ድረስ አባረሩአቸው በቁልቁለቱም ላይ ሳሉ መቱአቸው፤ የሕዝቡም ልብ ቀለጠ፥ እንደ ውኃም ሆነ።
መልሰውም ኢያሱን እንዲህ አሉት፦ “እኛ ባርያዎችህ ምድሪቱን ሁሉ እንዲሰጣችሁ፥ በእርሷም የሚኖሩትን ሁሉ ከፊታችሁ እንዲያጠፋ ጌታ አምላክህ ባርያውን ሙሴን እንዳዘዘ በእውነት ሰምተናል፥ ስለዚህም ከእናንተ የተነሣ ስለ ነፍሳችን እጅግ ስለ ፈራን ይህን ነገር አድርገናል።