La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢያሱ 17:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የእስራኤልም ልጆች በጸኑ ጊዜ ከነዓናውያንን የጉልበት ሥራ እንዲሠሩ አደረጉአቸው፥ ፈጽመውም አላሳደዱአቸውም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እስራኤላውያን በበረቱ ጊዜ ግን ከነዓናውያንን የጕልበት ሥራ እንዲሠሩ አስገደዷቸው እንጂ ከዚያ ፈጽመው አላባረሯቸውም ነበር።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እስራኤላውያን በኀይል እየበረቱ ቢሄዱም እንኳ ከነዓናውያንን ሁሉ አላባረሩአቸውም፤ ነገር ግን የጒልበት ሥራ እንዲሠሩላቸው ያስገድዱአቸው ነበር።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በረ​ቱ​ባ​ቸው፤ ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ን​ንም ገዙ​አ​ቸው፤ ነገር ግን ፈጽ​መው አላ​ጠ​ፉ​አ​ቸ​ውም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የእስራኤልም ልጆች በጸኑ ጊዜ ከነዓናውያንን የጉልበት ግብር አስገበሩአቸው፥ ፈጽመውም አላሳደዱአቸውም።

Ver Capítulo



ኢያሱ 17:13
13 Referencias Cruzadas  

ዕረፍትም መልካም መሆንዋን አየ፥ ምድሪቱም የለማች መሆንዋን፥ ትከሻውን ለመሸከም ዝቅ አደረገ፥ በከባድ ጉልበት ሥራ አገልጋይ ሆነ።


በዳዊት ቤትና በሳኦል ቤት መካከል የነበረው ጦርነት ለረጅም ጊዜ ቆየ፤ ሆኖም ዳዊት እያየለ ሲሄድ፥ የሳኦል ቤት ግን እየደከመ ነበር።


እስራኤላውያን ዘሮቻቸውን ለማጥፋት ያልቻሉትንና በምድሪቱ የቀሩትን እነዚህን እስከ ዛሬ እንደሚደረገው ሁሉ፥ ሰሎሞን ለግዳጅ ሥራ መለመላቸው።


በተረፈ በጌታ በኃይሉ ብርታትም ጠንክሩ።


ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን ነገር ማድረግ እችላለሁ።


በጌዝርም የተቀመጡትን ከነዓናውያንን አላሳደዱአቸውም፥ እስከ ዛሬም ድረስ ከነዓናውያን በኤፍሬም መካከል ተቀምጠዋል፤ እነርሱም የጉልበት ሥራ የሚሠሩ ባሮች ሆነዋል።


ነገር ግን በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ። ለእርሱ አሁንም ለዘለዓለምም ክብር ይሁን! አሜን።


እስራኤላውያን በበረቱ ጊዜ ግን ከነዓናውያንን የጉልበት ሥራ እንዲሠሩ አስገደዷቸው እንጂ ፈጽሞ አላስወጧቸውም።


ዛብሎንም እንደዚሁ በቂድሮንና በነህሎል የነበሩትን በመካከለቸው የቀሩትን ከነዓናውያንን አላስወጣም፤ ነገር ግን የጉልበት ሥራ እንዲሠሩ አስገደዳቸው።


ንፍታሌምም በቤትሳሚስና በቤትዓናት የሚኖሩትን አላስወጣም፤ ስለዚህ የንፍታሌም ነገድ በምድሪቱ ከሚኖሩት ከነዓናውያን ጋር አብረው ኖሩ፤ ይሁን እንጂ በቤትሳሚስና በቤትዓናት የሚኖሩት ለእነርሱ የጉልበት ሥራ ተገደው ይሠሩ ነበር።


አሞራውያን በሔሬስ ተራራና በኤሎን በሸዓልቢምም በመቀመጥ ጸኑ፥ ነገር ግን የዮሴፍ ቤት እጅ ከበደች፥ አስገበረቻቸውም።