La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዮሐንስ 8:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እነርሱም ይህን ሲሰሙ ከሽማግሌዎች ጀምሮ አንድ አንድ እያሉ ወጡ፤ ኢየሱስም ብቻውን ቀረ፤ ሴቲቱም በመካከል ቆማ ነበረች።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ይህን እንደ ሰሙ፣ ከሽማግሌዎች ጀምሮ አንድ በአንድ ወጡ፤ ሴትዮዋም እዚያው ፊቱ እንደ ቆመች ኢየሱስ ብቻውን ቀረ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እነርሱም ይህን በሰሙ ጊዜ ከሽማግሌዎች ጀምሮ ሁሉም አንድ በአንድ ከዚያ ሄዱ፤ ስለዚህ ኢየሱስ በመካከል ቆማ ከነበረችው ሴት ጋር ብቻውን ቀረ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እነ​ርሱ ግን ይህን በሰሙ ጊዜ ኅሊ​ና​ቸው ወቅ​ሶ​አ​ቸው ከሽ​ማ​ግ​ሌ​ዎች ጀምሮ እስከ ኋለ​ኞቹ ድረስ፥ አን​ዳ​ንድ እያሉ ወጡ፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ብቻ​ውን ቀረ፤ ሴት​ዮ​ዪ​ቱም በመ​ካ​ከል ቆማ ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እነርሱም ይህን ሲሰሙ ሕሊናቸው ወቀሳቸዋና ከሽማግሌዎች ጀምረው እስከ ኋለኞች አንድ አንድ እያሉ ወጡ፤ ኢየሱስም ብቻውን ቀረ ሴቲቱም በመካከል ቆማ ነበረች።

Ver Capítulo



ዮሐንስ 8:9
22 Referencias Cruzadas  

እርሷም ኤልያስን “የእግዚአብሔር ሰው ሆይ! ስለምን ይህን አደረግህብኝ? ወደዚህ የመጣኸው ኃጢአቴን አስታውሰህ ልጄ እንዲሞትብኝ ለማድረግ ነውን?” ስትል ጠየቀችው።


በአባቴ በንጉሥ ዳዊት ላይ የፈጸምከውን በደል ሁሉ በደንብ ታውቃለህ፤ አንተ ስላደረግኸው ክፉ ነገር ጌታ ራሱ ይቀጣሃል፤


ሰማይ በደሉን ይገልጥበታል፥ ምድርም ትነሣበታለች።


የክፉ ሰዎች ፉከራ አጭር መሆኑን አምላክን የሚክዱ ደስታቸው ቅጽበት መሆኑን አታውቁምን?


አቤቱ፥ ታድነኝ ዘንድ ፍቀድ፥ አቤቱ፥ እኔን ለመርዳት ፍጠን።


ይህን አድርገህ ዝም አልሁህ፥ እኔ እንደ አንተ የምሆን መሰለህ፥ እዘልፍሃለሁ በፊትህም እቆማለሁ።


ነፍሴን የሚቃወሙአት ይፈሩ ይጥፉም፥ ጉዳቴንም የሚፈልጉ እፍረትንና ኃሣርን ይልበሱ።


አንተ ደግሞ ሌሎችን የረገምክበትን ጊዜ ልብህ ያውቃልና።


ይህንንም ሲናገር የተቃወሙት ሁሉ አፈሩ፤ በእርሱም በተደረጉት ድንቅ ነገሮች ሁሉ ሕዝቡ በሙሉ ደስ አለው።


ኢየሱስም ቀና ብሎ “አንቺ ሴት! ከሳሾችሽ ወዴት አሉ? የፈረደብሽ የለምን?” አላት።


ደግሞም ኢየሱስ “እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም” ብሎ ተናገራቸው።


ማለዳም ደግሞ ወደ መቅደስ ደረሰ፤ ሕዝቡም ሁሉ ወደ እርሱ መጡ። ተቀምጦም ያስተምራቸው ነበር።


ጻፎችና ፈሪሳውያንም በምንዝር የተያዘችን ሴት ወደ እርሱ አመጡ፤ በመካከልም እርሱዋን አቁመው


ደግሞም ጐንበስ ብሎ በጣቱ በምድር ላይ ጻፈ።


ሕሊናቸው ሲመሰክርላቸው፥ እርስ በእርሳቸው ሐሳባቸው ሲካሰስ ወይም ሲከላከል፥ በልባቸው የተጻፈውን የሕግ ሥራ ያሳያሉ።


አታመንዝር የምትል ታመነዝራለህን? ጣዖቶችን የምትጠላ ቤተ መቅደሶችን ትዘርፋለህን?


ልባችን ቢወቅሰን እንኳ እግዚአብሔር ከልባችን ይልቅ ታላቅ ነውና ሁሉንም ያውቃል።