ዮሐንስ 18:37 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጲላጦስም “እንግዲያውስ ንጉሥ ነህን?” አለው። ኢየሱስም መልሶ “እኔ ንጉሥ እንደሆንሁ አንተ ትላለህ። እኔ ለእውነት ልመሰክር ተወልጃለሁ፤ ስለዚህም ወደ ዓለም መጥቻለሁ፤ ከእውነት የሆነ ሁሉ ድምፄን ይሰማል” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጲላጦስም፣ “ታዲያ፣ ንጉሥ ነህ ማለት ነዋ!” አለው። ኢየሱስም፣ “እኔ ንጉሥ እንደ ሆንሁ መናገርህ ትክክል ነው፤ የተወለድሁት፣ ወደዚህም ዓለም የመጣሁት ስለ እውነት ለመመስከር ነው፤ ከእውነት የሆነ ሁሉ ይሰማኛል” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጲላጦስም “ታዲያ፥ አንተ ንጉሥ ነኻ?” አለው። ኢየሱስም “እኔ ንጉሥ እንደ ሆንኩ አንተ ትላለህ፤ እኔ የተወለድኩትና ወደ ዓለም የመጣሁት ስለ እውነት ልመሰክር ነው፤ ከእውነት የሆነ ሁሉ ቃሌን ይሰማል” ሲል መለሰ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጲላጦስም፥ “እንግዲያ አንተ ንጉሥ ነህን?” አለው፤ ጌታችን ኢየሱስም መልሶ፥ “እኔ ንጉሥ እንደ ሆንሁ አንተ ራስህ ትላለህ፤ እኔ ስለዚህ ተወለድሁ፤ ስለዚህም ለእውነት ልመሰክር ወደ ዓለም መጣሁ፤ ከእውነት የሆነ ሁሉ ቃሌን ይሰማኛል” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጲላጦስም፦ “እንግዲያ ንጉሥ ነህን?” አለው። ኢየሱስም መልሶ፦ “እኔ ንጉሥ እንደ ሆንሁ አንተ ትላለህ። እኔ ለእውነት ልመሰክር ስለዚህ ተወልጃለሁ ስለዚህም ወደ ዓለም መጥቻለሁ፤ ከእውነት የሆነ ሁሉ ድምፄን ይሰማል” አለው። |
ኢየሱስም “አንተ አልህ፤ ነገር ግን እላችኋለሁ፥ ከእንግዲህ ወዲህ የሰው ልጅ በኃይል ቀኝ ሲቀመጥና በሰማይ ደመና ሲመጣ ታዩታላችሁ” አለው።
ኢየሱስ እንዲህ ሲል መለሰ፤ “እኔ ስለ እራሴ ምንም እንኳ ብመሰክር ከወዴት እንደመጣሁ ወዴትም እንድምሄድ አውቃለሁና ምስክርነቴ እውነት ነው፤ እናንተ ግን ከወዴት እንደመጣሁ ወዴትም እንደምሄድ አታውቁም።
እኛ ከእግዚአብሔር ነን፤ እግዚአብሔርን የሚያውቅ ይሰማናል፤ ከእግዚአብሔር ያልሆነ አይሰማንም። በዚህም የእውነትን መንፈስና የስሕተትን መንፈስ እናውቃለን።
የእግዚአብሔር ልጅ እንደመጣ፥ እውነት የሆነውን እንድናውቅ ማስተዋልን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነት በሆነው በእርሱ እንኖራለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘለዓለም ሕይወት ነው።
ከዮሐንስ በእስያ ላሉት ለሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት፤ ካለውና ከነበረው፥ ከሚመጣውም፥ በዙፋኑም ፊት ካሉት ከሰባቱ መናፍስት ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።
“በሎዲቅያም ወዳለው ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፥ አሜን የሆነው፥ የታመነውና እውነተኛው ምስክር፥ የእግዚአብሔርም ፍጥረት መጀመሪያ የነበረው እንዲህ ይላል፦