ኢዮብ 6:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በድሀ አደጉ ላይ ዕጣ ትጣጣላላችሁ፥ ለወዳጆቻችሁም ጉድጓድ ትቈፍራላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በድኻ አደጉ ላይ ዕጣ ትጣጣላላችሁን? ወይስ ወዳጃችሁን ትሸጣላችሁን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሙት ልጅ ላይ ዕጣ ትጣጣላላችሁ፤ ወዳጆቻችሁን ለመሸጥ የዋጋ ክርክር ታደርጋላችሁ! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በድሃ አደጉ ላይ ትስቃላችሁና፥ ወዳጃችሁንም ትሰድባላችሁና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በድሀ አደጉ ላይ ዕጣ ትጣጣላላችሁ፥ ለወዳጆቻችሁም ጕድጓድ ትቈፍራላችሁ። |
ለነፍሴ ጉድጓድ ቈፍረዋልና በውኑ በመልካም ፋንታ ክፉ ይመለሳልን? ስለ እነርሱ በመልካም ለመናገር ቁጣህንም ከእነርሱ ለመመለስ በፊትህ እንደ ቆምሁ አስታውስ።
ሆኖም ግን ተማርካ ተወሰደች፤ ሕፃናቶችዋ በመንገዶች ሁሉ ራስ ላይ ተፈጠፈጡ፤ በከበርቴዎችዋ ላይ ዕጣ ተጣጣሉ፥ ታላላቆችዋም ሁሉ በሰንሰለት ታሰሩ።
ለፍርድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ፤ በአስማተኞች፥ በዘማውያን፥ በሐሰት በሚምሉ፥ የሠራተኛውን ደመወዝ በሚያስቀሩ፥ መበለቲቱንና የሙት ልጅን በሚያስጨንቁ፥ ስደተኛውን በሚገፉ፥ እኔንም በማይፈሩ ላይ ፈጣን ምስክር እሆንባቸዋለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ።
በእግዚአብሔር አብ ፊት ንጹሕና ያልረከሰ አምልኮ፥ “አባትና እናት የሞቱባቸውን ልጆች፥ እንዲሁም ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶች በችግራቸው መርዳት፥ ራስንም ከዓለም ርኲሰት መጠበቅ ነው።”
ለገንዘብ ከመስገብገባቸው የተነሣ ራሳቸው ያዘጋጁትን ታሪክ እያወሩ ይበዘብዙአችኋል። ፍርዳቸውም ከብዙ ዘመን በፊት ጀምሮ ተዘጋጅቶላቸዋል፤ ጥፋትም በእርግጥ ይጠብቃቸዋል!