አቤቱ፥ በሰማይና በምድር ያለው ሁሉ የአንተ ነውና ታላቅነትና ኃይል፥ ክብርም፥ ድልና ግርማ ለአንተ ነው፤ አቤቱ፥ መንግሥት የአንተ ነው፥ አንተም በሁሉ ላይ ከፍ ከፍ ያልህ ራስ ነህ።
ኢዮብ 40:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ግርማንና ልዕልናን ተላበስ እንጂ፥ ሞገስንና ክብርን ተጐናጸፍ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲያስ ክብርንና ልዕልናን ተጐናጸፍ፤ ግርማ ሞገስንም ተላበስ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህ ከሆነ ራስህን በግርማ ሞገስ ተቀዳጅ ክብርንና ገናናነትንም ተጐናጸፍ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እስኪ ልዕልናንና ኀይልን ተላበስ፤ በክብርና በግርማም ተጐናጸፍ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በታላቅነትና በልዕልና ተላበስ፥ በክብርና በግርማም ተጐናጸፍ። |
አቤቱ፥ በሰማይና በምድር ያለው ሁሉ የአንተ ነውና ታላቅነትና ኃይል፥ ክብርም፥ ድልና ግርማ ለአንተ ነው፤ አቤቱ፥ መንግሥት የአንተ ነው፥ አንተም በሁሉ ላይ ከፍ ከፍ ያልህ ራስ ነህ።