ኢዮብ 4:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጥዋትና በማታ መካከል ይሰባበራሉ፥ ማንም ሳያስብ ለዘለዓለም ይጠፋሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በንጋትና በምሽት መካከል ይደቅቃሉ፤ ሳይታሰብም ለዘላለም ይጠፋሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በጠዋትና በማታ መካከል ይሰባበራሉ፤ ሳይታወቅ ለዘለዓለም ይጠፋሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከጥዋት እስከ ማታ አይኖሩም። ራሳቸውን ማዳንና መርዳት አይችሉምና ጠፉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በጥዋትና በማታ መካከል ይሰባበራሉ፥ ማንም ሳያስብ ለዘላለም ይጠፋሉ። |
መንገሥም በጀመረ ጊዜ የሠላሳ ሁለት ዓመት ጎልማሳ ነበረ፥ በኢየሩሳሌምም ስምንት ዓመት ነገሠ፤ ማንም ሳያዝንለት ከዚህ ዓለም በሞት ተሰናበተ፤ በዳዊትም ከተማ እንጂ በነገሥታቱ መቃብር አልቀበሩትም።