ኢዮብ 4:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይልቁንስ በጭቃ ቤት የሚኖሩ፥ መሠረታቸው በትቢያ ውስጥ የሆነ፥ ከብል በፊት የሚጨፈለቁ እንዴት ይሆኑ? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይልቁንስ በጭቃ ቤት የሚኖሩ፣ መሠረታቸው ከዐፈር የሆነ፣ ከብልም ይልቅ በቀላሉ የሚጨፈለቁ እንዴት ይሆኑ? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ታዲያ፥ ምስጥ ሳይበላቸው የሚፈርሱ መሠረታቸው ዐፈር በሆነና ከሸክላ በተሠራ ቤት ውስጥ በሚኖሩትማ ላይ እንዴት ይተማመንባቸዋል? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይልቁንም ከአንድ ዐይነት ጭቃ የተፈጠርን እኛ፥ በተፈጠርንበት የጭቃ ቤት የሚኖሩትን እንደ ብል ይጨፈልቃቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይልቁንስ በጭቃ ቤት የሚኖሩ፥ መሠረታቸው በትቢያ ውስጥ የሆነ፥ ከብል በፊት የሚጨፈለቁ እንዴት ይሆኑ? |
ከዚህ በኋላ ጌታ እግዚአብሔር ሰውን ከምድር አፈር አበጀው፥ በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት፥ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ።
የምንኖርበት ምድራዊ ድንኳን የሆነው ሕይወት ቢፈርስ፥ በሰማይ ዘላለማዊ የሆነ በእጅ ያልተሠራ፥ በእግዚአብሔር የታነጸ መኖሪያ እንዳለን እናውቃለን።