ኤልያስም “እኔስ የእግዚአብሔር ሰው ከሆንኩ እሳት ከሰማይ ወርዶ አንተንና ኀምሳውን ሰዎችህን ይብላ!” አለው፤ በዚያም ጊዜ ወዲያውኑ እሳት ከሰማይ ወርዶ መኰንኑንና ኀምሳዎቹን ሰዎች በላ።
ኢዮብ 38:35 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መብረቆች ሄደው፦ ‘እነሆ፥ እዚህ አለን’ ይሉህ ዘንድ፥ ልትልካቸው ትችላለህን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም መብረቆችን መስደድ ትችላለህ? እነርሱስ፣ ‘እነሆ፤ እዚህ አለን’ ይሉሃል? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መብረቅ በአንተ ትእዛዝ ይበርቃልን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መብረቁን ትልከዋለህን? እርሱስ ይሄዳልን? ደስታህስ ምንድን ነው ይልሃልን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መብረቆች ሄደው፦ እነሆ፥ እዚህ አለን ይሉህ ዘንድ፥ ልትልካቸው ትችላለህን? |
ኤልያስም “እኔስ የእግዚአብሔር ሰው ከሆንኩ እሳት ከሰማይ ወርዶ አንተንና ኀምሳውን ሰዎችህን ይብላ!” አለው፤ በዚያም ጊዜ ወዲያውኑ እሳት ከሰማይ ወርዶ መኰንኑንና ኀምሳዎቹን ሰዎች በላ።
ሙሴም እንዲህ አለው፦ “ከከተማ እንደ ወጣሁ እጄን ወደ ጌታ እዘረጋለሁ፤ ምድሪቱ የጌታ እንደ ሆነች እንድታውቅ፥ ነጎድጓዱ ይቆማል፥ በረዶውም ከእንግዲህ ወዲህ አይኖርም።