ኢዮብ 38:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሞት በሮች ተገልጠውልሃልን? የሞትንስ ጥላ ደጆች አይተሃልን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሞት ደጆች ተገልጠውልሃልን? የሞትንስ ጥላ በሮች አይተሃልን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሞትን በሮች እንድታይ ተደርገሃልን? የድቅድቅ ጨለማንስ መዝጊያ አይተሃልን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከግርማህስ የተነሣ የሞት በሮች ተከፍተውልሃልን? የሲኦል በረኞችስ አንተን አይተው ይደነግጣሉን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሞት በሮች ተገልጠውልሃልን? የሞትንስ ጥላ ደጆች አይተሃልን? |
ሰባቱን ከዋክብትና ኦሪዮን የተባለውን ኮበብ የፈጠረ፥ የሞትን ጥላ ወደ ንጋት የሚለውጥ፥ ቀኑንም በሌሊት የሚያጨልም፥ የባሕሩንም ውኆች ጠርቶ በምድር ፊት ላይ የሚያፈስሳቸው እርሱ፥ ስሙ ጌታ ነው።