ኢዮብ 36:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቃሌ በእውነት ሐሰት የለበትም፥ በእውቀትም ፍጹም የሆነ ከአንተ ጋር አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቃሌ ሐሰት እንዳልሆነ አረጋግጣለሁ፤ በዕውቀቱ ፍጹም የሆነ ሰው ከአንተ ጋራ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንግግሬ ሐሰት ላለመሆኑ እርግጠኛ ሁን፤ ከአንተ ጋር የምነጋገረው እኔ የተሟላ ዕውቀት እንዳለኝ ዕወቅ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቃሌ ሐሰት ያይደለ እውነት ነው። አንተም የዐመፅ ቃላትን አትሰማም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቃሌ በእውነት ያለ ሐሰት ነው፥ በእውቀትም ፍጹም የሆነ ከአንተ ጋር አለ። |
የእግዚአብሔርን ቃል ቀላቅለው እንደሚነግዱ እንደ ብዙዎቹ አይደለንም፤ በቅንነት ግን ከእግዚአብሔር እንደ ተላክን በእግዚአብሔር ፊት በክርስቶስ ሆነን እንናገራለን።
ከእናንተ ወገን የሆነ የክርስቶስ ባርያ ኤጳፍራ ሰላምታ ያቀርብላችኋል፤ በእግዚአብሔር ፈቃድ ሁሉ ተረድታችሁና ፍጹማን ሆናችሁ እንድትቆሙ፥ ሁልጊዜ ስለ እናንተ በጸሎቱ ይተጋል።