ኢዮብ 34:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክፋትን የሚሠሩ የሚደበቁበት ጨለማ ወይም የሞት ጥላ የለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክፉ አድራጊዎች የሚደበቁበት፣ ጨለማ ስፍራ ወይም የሞት ጥላ የለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ክፉ አድራጊዎች የሚደበቁበት፤ ድቅድቅ ጨለማ ከቶ የለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኀጢአትን የሚሠሩ የሚሰወሩበት ቦታ የለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኃጢአትን የሚሠሩ ይሰወሩበት ዘንድ ጨለማ ወይም የሞት ጥላ የለም። |
ሕዝብን አበዛህ፤ ደስታቸውንም ጨመርህ፤ ሰዎች ምርትን ሲሰበስቡ፤ ምርኮንም ሲከፋፈሉ ደስ እንደሚላቸው ሁሉ፤ እነርሱም በፊትህ ደስ ይላቸዋል።
ስለዚህም፥ በጨለማ የተሰወረውን ወደ ብርሃን የሚያወጣ ደግሞም የልብን ምክር የሚገልጥ ጌታ እስኪመጣ ድረስ፥ ጊዜው ሳይደርስ አንዳች አትፍረዱ፤ በዚያን ጊዜም እያንዳንዱ ምስጋናው ከእግዚአብሔር ዘንድ ይሆናል።