ደግሞም ጸሎቱ፥ ጌታም እንደ ተለመነው፥ ኃጢአቱና መተላለፉ ሁሉ፥ ራሱንም ሳያዋርድ የኮረብታው መስገጃዎችን የሠራበት የማምለኪያ ዐፀዱንና የተቀረጹትንም ምስሎች የተከለበት ስፍራ፥ እነሆ፥ በባለ ራእዮቹ ታሪክ መጽሐፍ ተጽፎአል።
ኢዮብ 33:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ እግዚአብሔር ይጸልያል፥ እርሱም ይሰማዋል፥ ፊቱንም በደስታ ያሳየዋል፥ ለሰውም የጽድቁን ዋጋ ይመልስለታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ እግዚአብሔር ይጸልያል፤ ሞገስም ያገኛል፤ የእግዚአብሔርን ፊት ያያል፤ ሐሤትም ያደርጋል፤ እግዚአብሔር ወደ ጽድቅ ቦታው ይመልሰዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ይጸልያል፤ ጸሎቱንም እግዚአብሔር ይሰማዋል የእግዚአብሔርን ፊት አይቶ ይደሰታል፤ እግዚአብሔርም ስለጽድቁ ዋጋውን ይከፍለዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ እግዚአብሔር ይጸልያል፥ ጸሎቱም ተቀባይነትን ያገኛል። በደስተኛም ፊት እያመሰገነ ይገባል፥ ለሰውም ጽድቁን ይመልስለታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ እግዚአብሔር ይጸልያል፥ እርሱም ሞገስን ይሰጠዋል፥ ፊቱንም በደስታ ያሳየዋል፥ ለሰውም ጽድቁን ይመልስለታል። |
ደግሞም ጸሎቱ፥ ጌታም እንደ ተለመነው፥ ኃጢአቱና መተላለፉ ሁሉ፥ ራሱንም ሳያዋርድ የኮረብታው መስገጃዎችን የሠራበት የማምለኪያ ዐፀዱንና የተቀረጹትንም ምስሎች የተከለበት ስፍራ፥ እነሆ፥ በባለ ራእዮቹ ታሪክ መጽሐፍ ተጽፎአል።
እነሆ፥ ይህን አላውቀውም ብትል፥ ልቦችን የሚመረምር እርሱ አያስተውልምን? ነፍስህንም የሚመለከት እርሱ አያውቅምን? ለሰውስ ሁሉ እንደ ሥራው አይመልስለትምን?
ጌታ ለእያንዳንዱ ሰው እንደ ጽድቁና እንደ ታማኝነቱ ይክፈለው። እኔ ግን ዛሬ አንተን ጌታ በእጄ አሳልፎ ሰጥቶኝ ሳለ ጌታ በቀባው ላይ እጄን አላነሣሁም።