አሳም በባለ ራእዩ ላይ ተቈጣ፤ ስለዚህም ነገር ተቈጥቶአልና በቊራኛ አስሮ በወህኒ ቤት አኖረው፤ በዚያን ጊዜም አሳ፥ ከሕዝቡ አያሌ ሰዎችን አሠቃየ።
ኢዮብ 33:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ደግሞ በአልጋ ላይ በስቃይ ይገሥጸዋል፥ አጥንቱም ሁሉ ያለማቋረጥ ይንቀጠቀጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ደግሞም ሰው ታምሞ በዐልጋው ላይ ሳለ፣ በዐጥንቱ የዘወትር ሥቃይ ይገሥጸዋል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወይም እንደገና ሰው በአጥንቱ ውስጥ በማያቋርጥ በሽታ በአልጋ ቊራኛነት እንዲገሠጽ ያደርጋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ደግሞ በአልጋ ላይ በደዌ ይገሥጸዋል፥ አጥንቱም ሁሉ ይንቋቋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞ በአልጋ ላይ በደዌ ይገሥጸዋል፥ አጥንቱንም ሁሉ ያደነዝዛል። |
አሳም በባለ ራእዩ ላይ ተቈጣ፤ ስለዚህም ነገር ተቈጥቶአልና በቊራኛ አስሮ በወህኒ ቤት አኖረው፤ በዚያን ጊዜም አሳ፥ ከሕዝቡ አያሌ ሰዎችን አሠቃየ።
ስለዚህም የማምለኪያ ዐፀዶችና የፀሐይ ምስሎች ዳግመኛ እንዳይነሡ የመሠዊያውን ድንጋይ ሁሉ እንደ ደቀቀ እንደ ኖራ ድንጋይ ባደረገ ጊዜ፥ እንዲሁ የያዕቆብ በደል ይሰረያል፥ ይህም ኃጢአትን የማስወገድ ፍሬ ነው።