ኢዮብ 29:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም፦ ‘በልጆቼ መካከል በክብር እሞታለሁ፥ ዕድሜዬንም እንደ አሸዋ አበዛለሁ፥’ እል ነበር፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እኔም በልቤ እንዲህ አልሁ፤ ‘ዘመኔ እንደ አሸዋ በዝቶ፣ በቤቴ ተደላድዬ እሞታለሁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ ‘ዕድሜዬ እንደ አሸዋ በዝቶ፥ በቤቴ እንዳለሁ በክብር እሞታለሁ’ ብዬ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም እንደምሸመግልና እንደማረጅ፥ እንደ ረዥም ዘንባባም ረዥም ዘመን እንደምኖር፥ እንደ አሸዋም ዘመኔን እንደማበዛ ዐሰብሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም አልሁ፦ በልጆቼ መካከል እሞታለሁ፥ ዕድሜዬንም እንደ አሸዋ አበዛለሁ፥ |
በዓለት ንቃቃት ውስጥ የምትቀመጥ፥ የተራራውን ከፍታ የምትይዝ ሆይ! ማሣቀቅያህና የልብህ ኩራት አታልለውሃል። ምንም እንኳ ጎጆህን እንደ ንስር ጎጆ ከፍ ብታደርግ፥ ከዚያ አወርድሃለሁ፥ ይላል ጌታ።