ጌታ ልቡ በእርሱ ዘንድ ፍጹም የሆነውን ለማጽናት ዐይኖቹ በምድር ሁሉ ይመለከታሉና። እንግዲህ አሁን የሞኞችን ተግባር ፈጽመሃል። ስለዚህም ከዛሬ ጀምሮ ጦርነት ይደረግብሃል።”
ኢዮብ 28:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም የምድርን ዳርቻ ይመለከታል፥ ከሰማይም በታች ያለውን ሁሉ ያያል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱ የምድርን ዳርቻ ይመለከታልና፤ ከሰማይ በታች ያለውንም ሁሉ ያያል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱም የምድርን ዳርቻ ሁሉ ይመለከታል፤ ከሰማይ በታች ያለውን ሁሉ ያያል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም በሰማይ ያለውን ይመለከታል፥ በምድርም ያለውን ሁሉ ያውቃል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም የምድርን ዳርቻ ይመለከታል፥ ከሰማይም በታች ያለውን ሁሉ ያያል። |
ጌታ ልቡ በእርሱ ዘንድ ፍጹም የሆነውን ለማጽናት ዐይኖቹ በምድር ሁሉ ይመለከታሉና። እንግዲህ አሁን የሞኞችን ተግባር ፈጽመሃል። ስለዚህም ከዛሬ ጀምሮ ጦርነት ይደረግብሃል።”
የዚህን የጥቂቱን ነገር ቀን የናቀ ማን ነው? በዘሩባቤል እጅ ቱንቢውን አይተው ይደሰታሉ። “እነዚህ ሰባቱም በምድር ሁሉ የሚዘዋወሩ የጌታ ዐይኖች ናቸው።”
በዙፋኑና በአራቱ ሕያዋን ፍጡራን መካከልም በሽማግሌዎችም መካከል እንደ ታረደ በግ ቆሞ አየሁ፤ ሰባትም ቀንዶችና ሰባት ዐይኖች ነበሩት፤ እነርሱም ወደ ምድር ሁሉ የተላኩ የእግዚአብሔር መናፍስት ናቸው።