ኢዮብ 24:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህስ ባይሆን ሐሰተኛ የሚያደርገኝ፥ ነገሬንስ እንደ ከንቱ የሚያደርገው ማን ነው?” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ይህ እንዲህ ካልሆነማ፣ የሚያስተባብለኝ ማን ነው? ቃሌን ከንቱ የሚያደርገውስ ማን ነው?” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደዚህ አይደለም ከተባለ እኔ ሀሰተኛ መሆኔንና የተናገርኩትም ቃል ትክክል አለመሆኑን የሚያረጋግጥ ማነው?” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህስ ባይሆን ሐሰተኛ ነህ የሚለኝ፥ ነገሬንስ እንደ ኢምንት የሚያደርገው ማን ነው?” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህስ ባይሆን ሐሰተኛ የሚያደርገኝ፥ ነገሬንስ እንደ ምናምን የሚያደርገው ማን ነው? |