ኢዮብ 23:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእኔ ላይ የወሰነውን ይፈጽማል፥ እንደዚህ ያሉ ብዙ ብያኔዎች እንዳሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእኔ ላይ የወሰነውን ይፈጽማል፤ ይህን የመሰለ ዕቅድም ገና ብዙ አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእኔ ላይ ያቀደውን ሁሉ ይፈጽመዋል፤ ይህንንም የሚመስሉ ብዙ ዕቅዶች አሉት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህም እኔ ስለ እርሱ ቸኰልሁ፤ በተገሠጽሁም ጊዜ አሰብሁት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእኔ ላይ የተወሰነውን ይፈጽማል፥ እንደዚህም ያለ ብዙ ነገር በእርሱ ዘንድ አለ። |
ደግሞም፦ “ሰዎችን የሚያሰናክል ድንጋይ የሚጥላቸውም ዓለት ሆነ፤” የሚሰናከሉት ቃሉን ባለመታዘዛቸው ነው፤ አስቀድመውም ለዚህ የተመደቡ ናቸው።