ኢዮብ 23:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግሬ ዱካውን ተከትሎአል፥ መንገዱንም ጠብቄአለሁ፥ ከመስመር አልወጣሁም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግሮቼ ርምጃውን በጥብቅ ተከታትለዋል፤ ፈቀቅ ሳልል መንገዱን ጠብቄአለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግሮቼ እርሱ በሚወደው መንገድ ይሄዳሉ፤ በማወላወል ወደ ግራም ወደ ቀኝም አልልም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንደ ትእዛዙ እወጣለሁ፥ መንገዱንም ጠብቄአለሁ፥ ፈቀቅም አላልሁም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግሬ ወደ እርምጃው ተጣብቆአል፥ መንገዱንም ጠብቄአለሁ፥ ፈቀቅም አላልሁም። |
ትምክህታችን ይህ ነው፦ በዚህ ዓለም ይልቁንም በእናንተ ዘንድ፥ በእግዚአብሔር ጸጋ እንጂ በሥጋዊ ጥበብ ባልሆነ፥ በእግዚአብሔር ቅድስናና ቅንነት እንደኖርን፥ የሕሊናችን ምስክርነት ነው።