ኢዮብ 22:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጹሑን ሰው ያድነዋል፥ በእጅህም ንጽሕና ትድናለህ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጎ ያልሆነውን ሰው እንኳ፣ ከአንተ እጅ ንጽሕና የተነሣ ያድነዋል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተም ቅን ልብ ያለህ ብትሆን እግዚአብሔር ከክፉ ሁሉ ይጠብቅሃል፤ እጆችህም ከበደል ሥራ የነጹ ቢሆኑ እግዚአብሔር ይታደግሃል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጹሕን ሰው ያድነዋል፤ በእጅህም ንጽሕና ትድናለህ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጹሑን ሰው ያድነዋል፥ በእጅህም ንጽሕና ትድናለህ። |
እጆቻቸሁን ለጸሎት ወደ እኔ ስትዘረጉ፤ ዐይኖቼን ከእናንተ እሰውራለሁ፤ አብዝታችሁ ብትጸልዩም እንኳ አልሰማችሁም፤ እጆቻችሁ በደም ተበክለዋል፤
በኢየሩሳሌም መንገድ እየተመላለሳችሁ ሩጡ፥ ተመልከቱም፥ እወቁም፥ በአደባባይዋም ፈልጉ፤ ፍርድን የሚያደርገውን እውነትንም የሚሻውን ሰው ታገኙ እንደሆነ ይቅር እላታለሁ።