ይህንን አይተው ጻድቃን ደስ ይላቸዋል፥ ንጹሑም ሰው ይስቅባቸዋል።
ጻድቃንም የእነዚያን ጥፋት አይተው ይደሰታሉ፤ ንጹሓንም እንዲህ ብለው ያፌዙባቸዋል፤
ክፉ ሰዎች ሲቀጡ በማየት ደጋግ ሰዎች ይደሰታሉ፤ ቀጥተኞች እንዲህ እያሉ በእነርሱ ላይ ያፌዛሉ፥
ጻድቃንም አይተው ሳቁ፤ ንጹሓንም በንቀት ይዘባበቱባቸዋል።
ጻድቃን ያዩታል፥ ደስም ይላቸዋል፥ ንጹሐንም በንቀት ይስቁባቸዋል።
ቅኖች ሰዎች በዚህ ነገር ይረበሻሉ፥ ንጹሕም አምላኩን በሚክድ ላይ ይበሳጫል።
መቅሠፍቱ ፈጥኖ ቢገድል፥ በንጹሐን ፈተና ይሳለቃል።
ቅኖች ያያሉ፥ ደስም ይላቸዋል፥ ክፋት በሙሉ አፉን ይዘጋል።
አምላክ ሆይ፥ እንደ ስምህ ምስጋናህም እንዲሁ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ነው፥ ቀኝህ ጽድቅን የተሞላች ናት።
የሚያጠፋ ቃልን ሁሉ፥ የሽንገላ ምላስን ወደድህ።
ድስታችሁ የእሾኽን መቀጣጠል ከመስማቱ በፊት፥ ሕያዋን ሳላችሁ በመዓቱ ጠራርጎ ያጠፋል።
ሰዎች ሁሉ ፈሩ፥ የእግዚአብሔርንም ሥራ ተናገሩ፥ ሥራውንም አስተዋሉ።
አቤቱ፥ ስለ ፍርድህ ጽዮን ሰምታ ደስ አላት፥ የይሁዳም ሴት ልጆች ደስ አላቸው፥
በጻድቃን ልማት ከተማ ደስ ይላታል፥ በክፉዎችም ጥፋት እልል ትላለች።
“ሰማይ ሆይ! ቅዱሳን፥ ሐዋርያትና ነቢያት ሆይ! ስለተፈረደባት በእርሷ ላይ ደስ ይበላችሁ፤ እግዚአብሔር ፈርዶላችኋልና።”