ኢዮአብም፥ “ከእንግዲህ በዚህ ሁኔታ ከአንተ ጋር ጊዜ ማጥፋት አልችልም” አለው፤ ስለዚህ በእጁ ሦስት ጦር ይዞ ሄደና አቤሴሎም እባሉጥ ዛፉ ላይ ተንጠልጥሎ ገና በሕይወት እያለ ወርውሮ በልቡ ላይ ተከላቸው።
ኢዮብ 20:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም ይመዝዘዋል፥ ከሥጋውም ይወጣል፥ ከሐሞቱም ብልጭ ብሎ ይሠርጻል፥ ፍርሃትም ይወድቅበታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀስቱን ከጀርባው፣ የሚያብለጨልጨውንም ጫፍ ከጕበቱ ይመዝዛል፤ ፍርሀትም ይይዘዋል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፍላጻውም ዘልቆ በስተጀርባው ይወጣል፤ የሚያብለጨልጨው ጫፉ ጒበቱን በጣጥሶ ያልፋል፤ በታላቅ ፍርሀትም ልቡ ይሸበራል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቀስቱም በሥጋው ውስጥ ያልፋል። ክፉም ነገር በሰውነቱ ይመላለሳል፤ ፍርሀትም ይወድቅበታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም ይመዝዘዋል፥ ከሥጋውም ይወጣል፥ ከሐሞቱም ብልጭ ብሎ ይሠርጻል፥ ፍርሃትም ይወድቅበታል። |
ኢዮአብም፥ “ከእንግዲህ በዚህ ሁኔታ ከአንተ ጋር ጊዜ ማጥፋት አልችልም” አለው፤ ስለዚህ በእጁ ሦስት ጦር ይዞ ሄደና አቤሴሎም እባሉጥ ዛፉ ላይ ተንጠልጥሎ ገና በሕይወት እያለ ወርውሮ በልቡ ላይ ተከላቸው።
እንግዲህ የጌታን ፍርሃት አውቀን፥ ሰዎችን ለማስረዳት እንጥራለን፤ ስለ ራሳችን ከሆነ በእግዚአብሔር ዘንድ የተገለጥን ነን፤ ለእናንተም ሕሊና የተገለጥን እንደ ሆንን ተስፋ አደርጋለሁ።