ኢዮብ 19:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይኸው ስትሰድቡኝ ዐሥር ጊዜ ነው፥ ስታሰቃዩኝም አላፈራችሁም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነሆ፤ ዐሥር ጊዜ ዘለፋችሁኝ፤ ያለ ዕፍረትም በደላችሁኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነሆ ዐሥር ጊዜ ትሰድቡኛላችሁ፤ ስታዋርዱኝም አታፍሩም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዐሥር ጊዜ ትናገሩኛላችሁ፥ ትሰድቡኛላችሁም፤ በሰውነቴ ላይ በጠላትነት ስትነሡብኝ አታፍሩም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይኸው ስትሰድቡኝ አሥር ጊዜ ነው፥ ስታሻክሩኝም አላፈራችሁም። |
ዮሴፍም ወንድሞቹን ገና ሲያያቸው ወዲያውኑ ዐወቃቸው፤ ነገር ግን እንደማያውቃቸው ሆኖ፥ “ከየት የመጣችሁ ናችሁ?” ብሎ በቁጣ ቃል ተናገራቸው። እነርሱም፥ “እህል፤ ለመሸመት ከከነዓን ምድር የመጣን ነን” ብለው መለሱለት።
የእንጀራችሁንም በትር በሰበርሁ ጊዜ፥ ዐሥር ሴቶች እንጀራችሁን በአንድ ምጣድ ይጋግራሉ፥ በሚዛንም መዝነው ዳግመኛ እንጀራችሁን ያመጡላችኋል፤ ትበላላችሁም ነገር ግን አትጠግቡም።
በግብጽ ምድርና በምድረ በዳ ያደረግሁትን ክብሬንና ተአምራቴን ያዩ እነዚህ ሰዎች ሁሉ ዐሥር ጊዜ እኔን ስለ ተፈታተኑኝ፥ ድምፄንም ስላልሰሙ፥