Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢዮብ 19:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 በእውነትም የሳትሁ እንደሆነ፥ ስሕተቴ ከእኔ ጋር ትኖራለች።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 በእውነት ተሳስቼ ከሆነ፣ ስሕተቱ የራሴ ጕዳይ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 በእርግጥ ተሳስቼ ከሆነ፥ ስሕተቱ የሚጐዳው ራሴን ብቻ ነው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 በእ​ው​ነት እኔ ከበ​ደ​ልሁ፤ ስሕ​ተቴ ከእኔ ጋር ትኖ​ራ​ለች። የማ​ላ​ው​ቀ​ው​ንም ነገር ተና​ገ​ርሁ፤ ነገ​ሬም ስን​ፍና ነው እንጂ በየ​ጊ​ዜው አይ​ደ​ለም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 በእውነትም የሳትሁ እንደ ሆነ፥ ስሕተቴ ከእኔ ጋር ትኖራለች።

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 19:4
8 Referencias Cruzadas  

ጠቢብ ብትሆን ለራስህ ጠቢብ ትሆናለህ፥ ፌዘኛም ብትሆን ፌዘኛነትህን ለብቻህ ትሸከማለህ። (የሚቀጥለው ከግሪክ የተጨመረ ነው።) ልጄ ለራስህ አዋቂ ብትሆን ለባልንጀራህም አዋቂ ትሆናለህ፥ ለራስህ ክፉ ብትሆን ግን ክፋትን ለብቻህ ትሸከማለህ። ሐሰትን የሚያዘጋጅ ሰው ነፋሳትን እንደሚገዛ ነው፥ የሚበርር ወፍንም እንደሚከተል ይመስላል። የወይኑ ቦታ መንገዱን ረስቷልና፥ የሚሠማራባትን መንገድ እንዲስት አድርጓልና፥ ወደ ምድረ በዳ ይሄዳል፥ ለጥም ወደ ተሠራች አገር ይሄዳል፥ የማያፈራ የማይጠቅም ገንዘብንም በእጁ ይሰበስባል።


እያንዳንዱ የገዛ ራሱን ሸክም ይሸከማልና።


መልካም ሆነ ወይም ክፉ፥ በሥጋችን እንደ ሠራነው ዋጋችንን ለመቀበል፥ ሁላችን በክርስቶስ የፍርድ ዙፋን ፊት እንቆማለን።


እነሆ ነፍሳት ሁሉ የእኔ ናቸው፥ የአባት ነፍስ የእኔ እንደ ሆነች የልጅም ነፍስ የእኔ ናት፥ ኃጢአት የምትሠራ ነፍስ እርሷ ትሞታለች።


ዳዊት ሕዝቡን የሚቀሥፈውን መልአክ ባየ ጊዜ ጌታን፥ “እነሆ፥ ኃጢአት የሠራሁት እኔ ነኝ! የተሳሳትሁም እኔ ነኝ! እነዚህ በጎች ግን ምን አጠፉ? እጅህ በእኔና በአባቴ ቤት ላይ እንድትሆን እለምንሃለሁ” አለ።


ይኸው ስትሰድቡኝ ዐሥር ጊዜ ነው፥ ስታሰቃዩኝም አላፈራችሁም።


በእውነትም ብትኩራሩብኝ፥ በመዋረዴም ብታሳብቡ፥


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios