ኢዮብ 19:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለምን እናንተ እንደ እግዚአብሔር ታሳድዱኛላችሁ? ከሥጋዬስ ስለምን አትጠግቡም?” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር እንዳሳደደኝ ለምን ታሳድዱኛላችሁ? አሁንም ሥጋዬ አልበቃችሁምን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዳሳደደኝ እናንተ ደግሞ ለምን ታሳድዱኛላችሁ? እስካሁንስ ያሠቃያችሁኝ አይበቃችሁምን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለ ምን እናንተ እንደ እግዚአብሔር ታሳድዱኛላችሁ? ከሥጋዬስ ስለምን አትጠግቡም? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለ ምን እናንተ እንደ እግዚአብሔር ታሳድዱኛላችሁ? ከሥጋዬስ ስለ ምን አትጠግቡም? |
ነፍስሽንም፦ “በአንቺ ላይ እንድንረማመድ ዝቅ በዪ” በሚሉአት በአስጨናቂዎችሽ እጅ አኖረዋለሁ፤ ጀርባሽንም ለሚሻገሩት እንደ መሬትና እንደ መንገድ አደረግሽላቸው።
የሕዝቤን ሥጋ በሉ፥ ቁርበታቸውን ከላያቸው ላይ ገፈፉ፥ አጥንታቸውን ሰበሩ፤ በአፍላል እንዳለ በድስትም ውስጥ እንደሚከተት ሥጋ ቆራርጠዋል።