Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢዮብ 19:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 እናንተ ወዳጆቼ ሆይ፥ ራሩልኝ፥ ራሩልኝ፥ የእግዚአብሔር እጅ መትታኛለችና።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 “ወዳጆቼ ሆይ፤ ራሩልኝ፤ የእግዚአብሔር እጅ መትታኛለችና ዕዘኑልኝ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 “ወዳጆቼ ሆይ! የእግዚአብሔር እጅ ስለ መታኝ እባካችሁ እናንተ እዘኑልኝ! ራሩልኝም!

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 እና​ንተ ወዳ​ጆቼ ሆይ፤ ማሩኝ፤ ማሩኝ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ ዳስ​ሳ​ኛ​ለ​ችና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 እናንተ ወዳጆቼ ሆይ፥ ማሩኝ፥ የእግዚአብሔር እጅ መትታኛለችና ማሩኝ።

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 19:21
13 Referencias Cruzadas  

ነገር ግን እጅህን ዘርግተህ ያለውን ሁሉ ዳስስ፥ በእውነት በፊትህ ይሰድብሃል።”


አቤቱ፥ በቁጣህ አትቅሠፈኝ፥ በመዓትህም አትገሥጸኝ።


እስረኞችን አብራችኋቸው እንደታሰረ ሆናችሁ አስቡ፤ እናንተም በሥጋ እንዳለ እያሰባችሁ የተጨነቁትንም እንደራሳችሁ አስቡ።


አንድም አካል ቢሠቃይ የአካል ክፍሎች ሁሉ ከእርሱ ጋር ይሠቃያሉ፤ አንድ አካልም ቢከበር የአካል ክፍሎች ሁሉ ከእርሱ ጋር ደስ ይላቸዋል።


ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ፤ ከሚያለቅሱ ጋር አልቅሱ።


“ቸርነትን ለወዳጁ የሚነፍግ፥ ሁሉን ቻይ አምላክን መፍራት የተወ ነው።


ሁሉን የሚችል የአምላክ ፍላጻ በሥጋዬ ውስጥ ነው፥ መርዙንም ነፍሴ ትጠጣለች፥ የእግዚአብሔር ሽብሮች በኔ ላይ ተሰልፈዋል።


እርሱ ግን፦ “አንቺ ከሰነፎች ሴቶች እንደ አንዲቱ ተናገርሽ፥ ከእግዚአብሔር እጅ መልካሙን ተቀበልን፥ ክፉ ነገርንስ አንቀበልምን?” አላት። በዚህ ሁሉ ኢዮብ በከንፈሩ አልበደለም።


ነገር ግን አሁን እጅህን ዘርግተህ አጥንቱንና ሥጋውን ዳስስ፥ በእውነት በፊትህ ይሰድብሃል።”


አሁንም፥ እነሆ፥ የጌታ እጅ በአንተ ላይ ናት፤ ዕውርም ትሆናለህ እስከ ጊዜውም ፀሐይን አታይም፤” አለው። ያን ጊዜም ጭጋግና ጨለማ ወደቀበት፤ በእጁም የሚመራውን እየዞረ ፈለገ።


እነርሱ እስኪያድጉ እስኪደርሱ መጠበቅ ትችላላችሁን? በእነርሱስ ምክንያት ባል ሳታገቡ ትቆያላችሁን? ልጆቼ ሆይ፥ እንዲህስ አይሆንም፥ እኔን ጌታ ተቈጥቶኛል፤ በእናንተም ላይ በደረሰው ነገር በጣም አዝኜአለሁ።”


አሁን ግን በአንተ ላይ መጥቷል፥ አንተም ደከምህ፥ ደርሶብሃል፥ አንተም ተረበሽህ።


ዘወትር ቀኑን ሁሉ እጁን በላዬ መለሰ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios