ኢዮብ 19:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሠራዊቱ አብረው መጡ፥ መንገዳቸውንም በላዬ አዘጋጁ፥ በድንኳኔም ዙሪያ ሰፈሩ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰራዊቱ ገፍተው መጡ፤ በዙሪያዬ ምሽግ ሠሩ፤ ድንኳኔንም ከብበው ሰፈሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔን ለማጥፋት ሠራዊቱን ላከ፤ በድንኳኔም ዙሪያ ምሽግ ሠርተው ከበቡኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሠራዊቱ አብረው በእኔ ላይ መጡ፥ የሚሸምቁብኝም መንገዴን ከበቡ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሠራዊቱ አብረው መጡ፥ መንገዳቸውንም በላዬ አዘጋጁ፥ በድንኳኔም ዙሪያ ሰፈሩ። |
ነፍስሽንም፦ “በአንቺ ላይ እንድንረማመድ ዝቅ በዪ” በሚሉአት በአስጨናቂዎችሽ እጅ አኖረዋለሁ፤ ጀርባሽንም ለሚሻገሩት እንደ መሬትና እንደ መንገድ አደረግሽላቸው።