በዚህና በዚያም አፈረሰኝ፥ እኔም ሄድሁ፥ ተስፋዬንም እንደ ዛፍ ነቀለው፥
እስክወገድ ድረስ በሁሉ አቅጣጫ አፈራርሶኛል፤ ተስፋዬንም እንደ ዛፍ ነቅሎታል።
ሰውነቴን በየአቅጣጫው በመቀጥቀጥ ጨርሶ አፈራረሰው፤ የነበረኝንም ተስፋ ሥሩ ተነቃቅሎ እንደሚወድቅ ዛፍ አደረገው።
በዚህና በዚያ አፈረሰኝ፤ እኔም ሄድሁ፤ ተስፋዬንም እንደ ዛፍ ቈረጠው።
እነሆ፥ ካፈረሰ፥ የፈረሰው ተመልሶ አይሠራም፥ በሰውም ላይ ከዘጋ፥ ሊከፈት አይችልም።
ውኆች ድንጋዮቹን ይፍቃሉ፥ ፈሳሾቹም የምድሩን አፈር ይወስዳሉ፥ እንዲሁም የሰውን ተስፋ ታጠፋዋለህ።
ቀኖቼ አለፉ፥ ዕቅዴና የልቤ ምኞት ቀለጠ።
እንግዲህ ተስፋዬ ወዴት ነው? ተስፋዬንስ የሚያይ ማን ነው?
ሰይጣንም ከጌታ ፊት ወጣ፥ ኢዮብንም ከእግሩ መርገጫ ጀምሮ እስከ አናቱ ድረስ በክፉ ቁስል መታው።
ማኅፀን ትረሳዋለች፥ ትልም በደስታ ይጠባዋል፥ ዳግመኛም የሚያስታውሰው የለም፥ ክፋትም እንደ ዛፍ ይሰበራል።”
እጠብቅ ዘንድ ጉልበቴ ምንድነው? እታገሥም ዘንድ ፍጻሜዬ ምንድነው?
ቀኖቼ ከሸማኔ መወርወርያ ይልቅ ይቸኩላሉ፥ ያለ ተስፋም ያልቃሉ።”
ከቁጣህና ከመዓትህም የተነሣ፥ አንሥተኸኛልና፥ ጥለኸኝማልና።