ይህ ከፍ ከፍ ብሎ የሚታየው ቤተ መቅደስ ፈርሶ የፍርስራሽ ክምር ይሆናል፤ በዚያ በኩል የሚያልፉ ሰዎች ይህን አይተው በመደንገጥ ‘እግዚአብሔር ይህን አገርና ይህን ቤተ መቅደስ ለምን እንዲህ አደረገ?’ በማለት ይሳለቁበታል።
ኢዮብ 18:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የፊተኞች ሰዎች እንደ ደነገጡ፥ እንዲሁ የኋለኞች ሰዎች ስለ ዘመኑ ይደነቃሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባጋጠመው ሁኔታ የምዕራብ ሰዎች ይደነግጣሉ፤ የምሥራቅም ሰዎች በፍርሀት ይዋጣሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የምዕራብና የምሥራቅ ሰዎች በእርሱ ላይ በደረሰው መከራ እጅግ ፈርተው ተንቀጠቀጡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ባዕድ በንብረቱ ላይ ተድላ ያደርጋል፤ ድሃው በእርሱ ያጕረመርማል። ፊተኞቹም ይደነቃሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የፊተኞች ሰዎች እንደ ደነገጡ፥ እንዲሁ የኋለኞች ሰዎች ስለ ዘመኑ ይደነቃሉ። |
ይህ ከፍ ከፍ ብሎ የሚታየው ቤተ መቅደስ ፈርሶ የፍርስራሽ ክምር ይሆናል፤ በዚያ በኩል የሚያልፉ ሰዎች ይህን አይተው በመደንገጥ ‘እግዚአብሔር ይህን አገርና ይህን ቤተ መቅደስ ለምን እንዲህ አደረገ?’ በማለት ይሳለቁበታል።
አንቺንም በአንቺም ውስጥ የሚኖሩትን ልጆችሽን በምድር ላይ ይጨፈልቃሉ፤ በአንቺ ውስጥም በድንጋይ ላይ የሚኖር ድንጋይ አያስቀሩም፤ የተጐብኘሽበትን ዘመን አላወቅሽምና።”