አሁን ግን እርምጃዬን ቈጥረኸዋል፥ ይልቁንም ኃጢአቴን ባልተጠባበቅህ።
በዚያ ጊዜ በርግጥ ርምጃዬን ትከታተላለህ፤ ነገር ግን ኀጢአቴን አትቈጣጠርም።
እነሆ አሁን እርምጃዬን ሁሉ ትከታተላለህ፤ ሆኖም ኃጢአቴን አታስብብኝም።
አሁን ግን ኀጢአቶችን ቈጥረሃል፤ ከበደሌም እንዲቱንስ እንኳ አልረሳህም።
አሁን ግን እርምጃዬን ቈጥረኸዋል፥ ኃጢአቴንም ትጠባበቃለህ።
ኃጢአት ብሠራ አንተ ትመለከተኛለህ፥ ከኃጢአቴም ንጹሕ አታደርገኝም።
ታዲያ ክፋቴን የምትከታተለው፥ ኃጢአቴንም የምትመረምረው ለምንድን ነው?
እግሬንም በእግር ግንድ አግብተሃል፥ መንገዴንም ሁሉ ተቆጣጥረሃል፥ የእግሬንም ዱካ ወስነሃል።
መንገዴን አያይምን? እርምጃዬንስ ሁሉ አይቈጥርምን?”
እግሬን በግንዶች መካከል ያጣብቃል፥ መንገዶቼን ሁሉ ይቆጣጠራል።’
ዐይኖቹ የሰውን መንገድ ይመለከታሉ፥ የሰውን እርምጃ በሙሉ ያያል።
ሁልጊዜ ቃሎቼን ይጠመዝዙብኛል፥ በእኔ ላይም የሚመክሩት ሁሉ ለክፉ ነው።
የሰው መንገድ በጌታ ፊት ነውና፥ አካሄዱንም ሁሉ እርሱ ይመለከታልና።
በምክር ታላቅ በሥራም ብርቱ ነህ፤ ለሁሉም እንደ መንገዱና እንደ ሥራው ፍሬ ለመስጠት ዐይኖችህ በአዳም ልጆች መንገድ ሁሉ ተገልጠዋል።