እጅህን ከእኔ አርቅ፥ ግርማህም አታስደንግጠኝ።
እጅህን ከእኔ ላይ አንሣ፤ በግርማህም አታስፈራራኝ፤
ይኸውም የቅጣት ክንድህን ከእኔ ላይ አንሣ፤ አስፈሪ በሆነው ግርማህ አታስደንግጠኝ።
እጅህን ከእኔ አርቅ፤ ግርማህም አታስደንግጠኝ።
የሕይወቴ ቀኖች ጥቂት አይደሉምን?
ክብሩስ አያስፈራችሁምን? ግርማውስ አይወድቅባችሁምን?
ነገር ግን ሁለት ነገሮችን አድርግልኝና፥ የዚያን ጊዜ ከፊትህ አልሰወርም፥
እነሆ፥ ግርማዬ አያስፈራህም፥ እኔም አልጫንህም።”
በትሩን ከእኔ ላይ ያርቅ፥ ግርማውም አያስፈራኝ፥
ሥጋዬ አንተን ከመፍራት የተነሣ ደነገጠ፥ ከፍርድህ የተነሣ ፈርቻለሁ።
አንተ ሠርተኸኛልና ዝም አልሁ አፌንም አልከፈትሁም።
ነገር ግን እጄን መለስሁ፥ በፊታቸውም ባወጣኋቸው በአሕዛብ ፊት ስሜ እንዳይረክስ ብዬ ስለ ስሜ ሠራሁ።