ኢዮብ 11:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር ልትመረምር ትችላለህን? ሁሉን የሚችል አምላክን ፍጻሜ ልትመረምር ትችላለህን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የእግዚአብሔርን ጥልቅ ምስጢር ልትለካ ትችላለህን? ወይስ ሁሉን ቻዩን አምላክ መርምረህ ትደርስበታለህን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የእግዚአብሔርን ጥልቅ ምሥጢር ማወቅ ትችላለህን? ሁሉን ቻይ አምላክንስ መርምረህ ልትደርስበት ትችላለህን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የእግዚአብሔርን ፍለጋ ልትመረምር ትችላለህን? ወይስ ሁሉን የሚችል አምላክ ወደ ፈጠረው ፍጥረት ፍጻሜ ትደርሳለህን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር ልትመረምር ትችላለህን? ወይስ ሁሉን የሚችል አምላክን ፈጽመህ ልትመረምር ትችላለህን? |
ወደ ሰማይ የወጣ የወረደስ ማን ነው? ነፋስንስ በእጁ የጨበጠ ማን ነው? ውኃንስ በልብሱ የቋጠረ ማን ነው? የምድርን ዳርቻ ሁሉ ያጸና ማን ነው? ይህን ታውቅ እንደሆንህ፥ ስሙ ማን የልጁስ ስም ማን ነው?
ነገርን ሁሉ በጊዜው ውብ አድርጎ ሠራው፤ እግዚአብሔርም ከጥንት ጀምሮ እስከ ፍጻሜ ድረስ የሠራውን ሥራ ሰው መርምሮ እንዳያገኝ ዘላለማዊነትን በልቡ ሰጠው።
ሁሉም ነገር በአባቴ ለእኔ ተሰጥቶአል፤ ከአብ በቀር ወልድን የሚያውቅ የለም፤ ከወልድና ወልድም ሊገለጥለት ከሚፈቅደው በቀር አብን የሚያውቅ የለም።