ኢዮብ 11:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከንቱ ልፍለፋህ ሰዎችን ዝም ያሰኛቸዋልን? ብትሳለቅስ የሚያሳፍርህ የለምን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም በውኑ የአንተ መዘላበድ ሰውን ዝም ያሰኛልን? ስታፌዝስ የሚገሥጽህ የለም? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢዮብ ሆይ! ከንቱ ንግግርህ መልስ የማይሰጥበት ይመስልሃልን? ይህን ያኽልስ ስታፌዝ፥ የሚገሥጽህ የሌለ መሰለህን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንግግር አታብዛ፤ የሚከራከርህ የለምና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ትምክህትህስ ሰዎችን ዝም ያሰኛቸዋልን? ብትሳለቅስ የሚያሳፍርህ የለምን? |
ኢዮብም፦ በእግዚአብሔር መደሰት ለሰው ምንም አይጠቅምም ብሏልና፥ ከበደለኞች ጋር የሚተባበር፥ ክፉ ከሚያደርጉስ ጋር የሚሄድ፥ ሹፈትን እንደ ውኃ የሚጠጣት እንደ ኢዮብ ያለ ሰው ማን ነው?”