Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ተሰሎንቄ 3:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 በዚህ መልእክት በኩል ለተላከው ቃላችን የማይታዘዝ ማንም ቢኖር፥ ይህን ሰው በምልክት ለዩት፤ እንዲያፍርም ከእርሱ ጋር አትተባበሩ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 በዚህ መልእክት ላይ ላለው ቃላችን የማይታዘዝ ማንም ቢኖር፣ እንደዚህ ያለውን ሰው በጥንቃቄ ተከታተሉት፤ በሥራውም እንዲያፍር ከርሱ ጋራ አትተባበሩ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 በዚህ መልእክት ያስተላለፍንላችሁን ምክር የማይቀበል ሰው ቢኖር እንዲህ ያለውን ሰው ልብ በሉት፤ እንዲያፍርም ከእርሱ ጋር ግንኙነት አታድርጉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 በዚህ መልእክት ለተላከ ቃላችን የማይታዘዝ ማንም ቢኖር፥ ይህን ተመልከቱት፤ ያፍርም ዘንድ ከእርሱ ጋር አትተባበሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 በዚህ መልእክት ለተላከ ቃላችን የማይታዘዝ ማንም ቢኖር፥ ይህን ተመልከቱት፥ ያፍርም ዘንድ ከእርሱ ጋር አትተባበሩ።

Ver Capítulo Copiar




2 ተሰሎንቄ 3:14
29 Referencias Cruzadas  

እንዲህም አልሁ፦ “አምላኬ ሆይ፥ አፍሬአለሁ፤ አምላኬ ሆይ፥ ፊቴንም ወደ አንተ ለማንሣት እፈራለሁ፥ ኃጢአታችን ከራሳችን በላይ ከፍ ብሏልና፥ በደላችንም ወደ ሰማያት ወጥቷልና።


እንዲሁ በቁጣህ አሳድዳቸው፥ በመቅሠፍትህም አስደንግጣቸው።


የአስተማሪዎቼንም ቃል አልሰማሁም፥ ጆሮቼንም ወደ አስተማሪዎቼ አላዘነበልሁም።


ስለዚህ ካፊያ ተከለከለ፥ የበልጉም ዝናብ ጠፋ፤ የጋለሞታም ሴት ፊት ቢኖርሺም እንኳ ለማፈር ግን እንቢ አልሽ።


ርኩስን ነገር ስለ ሠሩ አፍረዋልን? ምንም አላፈሩም፥ እፍረትንም አላወቁም፤ ስለዚህ ከሚወድቁ ጋር ይወድቃሉ፤ በጐበኘኋቸው ጊዜ ይዋረዳሉ፥” ይላል ጌታ።


ማንንም አታዳምጥም፥ እርምት አትቀበልም፥ በጌታ አልታመነችም፥ ወደ አምላክዋም አልቀረበችም።


ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “አባትዋ ምራቁን በፊትዋ ቢተፋባት እንኳ እርሷ ሰባት ቀን ልታፍር አይገባትምን? ሰባት ቀን ከሰፈሩ ውጪ ተዘግቶባት ትቀመጥ፥ ከዚያም በኋላ ትመለስ።”


እነርሱንም ባይሰማ፥ ለቤተ ክርስቲያን ንገራት፤ ቤተ ክርስቲያንንም ባይሰማት፥ እንደ አረመኔና እንደ ቀራጭ ቁጠረው።


ወንድሞች ሆይ! ከሚለያዩትና እናንተ የተማራችሁትን ትምህርት በመቃወም መሰናክል ከሚያደርጉ ሰዎች እንድትጠነቀቁ አሳስባችኋለሁ፤ ከእነርሱም ራቁ፤


እንደምወዳችሁ ልጆቼ አድርጌ ልገሥጻችሁ እንጂ ላሳፍራችሁ ይህን አልጽፍም።


አሁን ግን ወንድሞች ከሚባሉት አንዱ ሴሰኛ ወይም ስግብግብ ወይም ጣዖትን የሚያመልክ ወይም ተሳዳቢ ወይም ሰካራም ወይም ነጣቂ ቢሆን ከእርሱ ጋር እንዳትተባበሩ እጽፍላችኋለሁ፤ እንደዚህ ካለው ጋር መብል እንኳን አትብሉ።


በመልእክቴ ከሴሰኞች ጋር እንዳትተባበሩ ጻፍሁላችሁ።


መታዘዛችሁም በተፈጸመች ጊዜ አለመታዘዝን ሁሉ ልንበቀል ተዘጋጅተናል።


በሁሉ የምትታዘዙ እንደ ሆናችሁ የእናንተን መፈተን ለማወቅ በማሰብ፥ ስለዚህ ደግሞ ጽፌ ነበር።


ስለዚህም በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ እንዴት እንደ ተቀበላችሁት፥ የሁላችሁን መታዘዝ እያሰበ ለእናንተ ያለው ፍቅር እጅግ ጨምሯል።


አንተም በግብጽ ባርያ እንደ ነበርክ አስታውስ፤ ይህንንም ሥርዓት በጥንቃቄ ጠብቅ።


ስለዚህ ወዳጆቼ ሆይ! ሁልጊዜ እንደ ታዘዛችሁ፥ በእናንተ ዘንድ በመኖሬ ብቻ ሳይሆን ይልቁን አሁን ስርቅ ይበልጥ በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ፤


ይህም መልእክት በእናንተ ዘንድ ከተነበበ በኋላ፥ በሎዶቅያ ሰዎች ማኅበር ደግሞ እንዲነበብ አድርጉ፤ ከሎዶቅያም የምታገኙትን መልእክት እናንተ ደግሞ አንብቡ።


ስለዚህ ይህን የማይቀበል፥ የማይቀበለው፥ ሰውን ሳይሆን፥ ቅዱስ መንፈሱን ደግሞም የሰጠንን እግዚአብሔርን ነው።


ወንድሞች ሆይ! ከእኛ እንደ ተቀበሉት ትውፊት ሳይሆን ሥራን በመፍታት ከሚኖሩ ወንድሞች ሁሉ እንድትለዩ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናዛችኋለን።


የሚቃወም ሰው ስለ እኛ የሚናገረውን መጥፎ ነገር ሲያጣ እንዲያፍር እውነተኛና የማይነቀፍ ቃልን ተናገር።


መለያየትን የሚያሥነሣ ሰው አንዴና ሁለቴ ከገሠጽኸው በኋላ እንዲህ ከሚመስል ሰው ራቅ።


ከምጠይቅህ ይልቅ አብልጠህ እንደምታደርግ በማወቅ እንደምትታዘዝም በመተማመን እጽፍልሃለሁ።


ለመሪዎቻችሁ ታዘዙ፤ ተገዙላቸውም። እነርሱ እንደሚጠየቁበት አድርገው ስለ ነፍሳችሁ ይተጋሉ፤ ይህንንም በደስታ እንጂ በኀዘን እንዳያደርጉት፥ አለበለዚያ አይጠቅማችሁም።


ማንም ወደ እናንተ ቢመጣ ይህንም ትምህርት ባያመጣ በቤታችሁ አትቀበሉት፤ ሰላምም አትበሉት፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos