ኤርምያስ 9:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እነሆ፥ ሸለፈታቸውን ብቻ የተገረዙትን ሁሉ የምቀጣበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል ጌታ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ሥጋቸውን ብቻ የተገረዙትን ሁሉ የምቀጣበት ጊዜ ይመጣል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ለስም ብቻ የተገረዙትን ሁሉ የምቀጣበት ጊዜ ይመጣል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እነሆ ዘመን ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር። የተገረዙትንና ያልተገረዙትን ሁሉ በአንድነት እጐበኛለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሕዛብ ሁሉ ያልተገረዙ ናቸውና፥ የእስራኤልም ቤት ሁሉ ልባቸው ያልተገረዘ ነውና የተገረዙትን ሁሉ፥ ግብጽንና ይሁዳን ኤዶምያስንም የአሞንንም ልጆች ሞዓብንም በምድረ በዳም የተቀመጡትን ጠጕራቸውን በዙሪያ የተላጩትን ሁሉ፥ ባለመገረዛቸው እነርሱን የምቀጣበት ዘመን እነሆ ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር። |
እናንተም የይሁዳ ሰዎች በኢየሩሳሌምም የምትኖሩ ሆይ! ስለ ሥራችሁ ክፋት ቁጣዬ እንደ እሳት እንዳይወጣ የሚያጠፋውም ሳይኖር እንዳያቃጥል፥ ለጌታ እራሳችሁን ግረዙ፥ የልባችሁንም ሸለፈት አስወግዱ።”
ግመሎቻቸው ይበዘበዛሉ የእንስሶቻቸውም ብዛት ይማረካል፤ ጠጉራቸውንም ዙሪያውን የተላጩትን ሰዎች ወደ ነፋሳት ሁሉ እበትናቸዋለሁ፤ ከሁሉም አቅጣጫ ጥፋት አመጣባቸዋለሁ፥ ይላል ጌታ።
በክብርና በታላቅነት ከዔድን ዛፎች መካከል እንግዲህ ማንን ትመስላለህ? ሆኖም ከዔድን ዛፎች ጋር ወደ ታችኛው ምድር ትወርዳለህ፥ በሰይፍ በተገደሉት ባልተገረዙት መካከል ትጋደማለህ። ይህም ፈርዖንና ብዛቱ ሁሉ ነው፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
ምግቤን፥ ስብንና ደምን፥ በምታቀርቡበት ጊዜ ቤቴን እንዲያረክሱ በመቅደሴ ውስጥ እንዲሆኑ ያልተገረዘ ልብ፥ ያልተገረዘ ሥጋ ያላቸውን ባዕዳንን አግብታችኋል፥ በርኩሰታችሁም ሁሉ ቃል ኪዳኔን አፍርሰዋል።
እኔም ደግሞ እነርሱን በመቃወም እሄዳለሁ፤ ወደ ጠላቶቻቸውም ምድር አመጣቸዋለሁ፤ ነገር ግን በዚያን ጊዜ ያልተገረዘው ልባቸው ቢዋረድ፥ የበደላቸውንም ቅጣት ቢቀበሉ፥
ነገር ግን በስውር አይሁዳዊ የሆነ አይሁዳዊ ነው፤ መገረዝም በመንፈስ የሆነ የልብ መገረዝ ነው እንጂ በፊደል አይደለም፤ ምስጋናውም ከእግዚአብሔር ነው እንጂ ከሰው አይደለም።
ዮናታን ወጣት ጋሻ ጃግሬውን፥ “ና፤ ወደነዚያ ያልተገረዙ ሰዎች ጦር ሰፈር እንሻገር፤ ምናልባትም ጌታ ይዋጋልን ይሆናል፤ በብዙም ሆነ በጥቂት ለማዳን ጌታን የሚያግደው የለምና” አለው።
ዳዊት በአጠገቡ የቆሙትን ሰዎች፥ “ይህን ፍልስጥኤማዊ ገድሎ እንዲህ ያለውን ውርደት ከእስራኤል ለሚያስወግድ ሰው ምን ይደረግለታል? ደግሞስ የሕያው እግዚአብሔርን ሠራዊት ይገዳደር ዘንድ ይህ ያልተገረዘ ፍልስጥኤማዊ እርሱ ማነው?” ሲል ጠየቀ።